ማሻ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ጥራት ያለውን አገልግሎት መስጠት እንዲችል የድጋፍና ክትትል ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ።
በሸካ ዞን በማሻ ከተማ በቅርቡ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ለሆነዉ ለማሻ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከ5 መቶ ሽህ ብር በላይ የሚገመት የመድሀኒትና የህክምና መገልገያ ግብዓቶች ድጋፍ ማድረጉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል። የክልሉ ጤና ቢሮ በህክምና አገልግሎቶች ዘርፍ የመድሀኒትና የህክምና መሳሪያዎች አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አበበ ከበደ እንደገለጹት የማሻ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የግንባታ ስራ…