ዳውሮ ዞን ማሪ ማንሳ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት በ44 ቀናት ውስጥ የተሰራ የወባ ወረርሽኝ መከላከልና መቆጣጠር ዘመቻ ሥራዎች አፈፃፀም ገመገመ።
እንደ ወረዳችን እየተስተዋለ ያለውን ከፍተኛ የወባ ስርጭትን ለመግታት የተለያዩ በመከላከል ሥራዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በረከት ባቡሎ ተናግሯል። የወባ በሽታው የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የተደረጉ ርብርብ እና የተቀናጀ የዘመቻ ሥራ አበረታች ቢሆንም ማኅበረሰቡን በተደራጀ ሁኔታ በማሳተፍ ባለቤትነትን በመፍጠር የወባ አስተላላፊ ትንኝ ቁጥጥር ሥራ መሰራት እንዳለበትም ተገምግሟል። በ44 ቀናት በተደረገው…