የወባን ስርጭት ለመከላከል ከወትሮ በተለየ መስራት እንደሚገባ የማጂ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት አስታወቀ።
ጽ/ቤቱ በዛሬው ዕለት ከጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ጋር ባካሄደው ውይይት መድረክ ላይ የኩብት፣ የቀይኮከብ፣ የኦር፣ የሻልት እና የገልከም ቀበሌዎች አፈፃፀም የቀረበ ሲሆን በጥንካሬ የተለዩ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እንዲሁም በጉድለት የታዩ ትኩረት ተደርጎባቸው ሊፈፀሙ እንደሚገባ ተገልጿል። የማጂ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ አምሳል ወ/ገብርዔል እንደገለፁት የጤና መረጃ አያያዝና አላላክ ሥርዓታችንን በማሻሻል የመረጃ መፋለስን ለማስቀረት በትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።…