ህብረተሰቡ ባለመዘናጋት ራሱን ከወባ ወረርሽኝ መከላከል እንዳለበት ተገለጸ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ም/ቤት ምክትል አፌ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፀሀይ ዳርጫ የተመራ ሉካን ቡድን በዳውሮ ዞን ገና ወረዳ የወባ ወረርሽኝ መከላከል ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደዋል ።
የወባ በሽታ ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ ሥራዎችን መስራት እንደሚገባ ያነሱት የተከበሩ ወ/ሮ ፀሀይ በተለይ የመከላከል ሥራውን ውጤታማ ለማድረግ የህብረተሰቡ ተሳትፎ እና የግንዛቤ ሥራ በሁሉም ቀበሌ ትምህርት መሰጠት እንደሚገባ አሳስበዋል ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ በሸታ መከላከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶክተር እንዳለ ሳህሌ እንደገለጹት በተለይ በክልላችን የተከሰተው የወባ ወረርሽኝ ለመቆጣጠርና የሚያደርሰውን ጉዳትን ለመቀነስ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ጎን ለጎን ሁሉም የራሱን እና የአከባቢ ንጽሕና መጠበቅ አለባቸው ብለዋል።
ወረርሽኙን ለመከላከል የወባ የትንኝ ቁጥጥር ፣መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ የማህበረሰብ ተሳትፎና ግንዛቤ የሚያሳድጉ ስራዎችን መሥራት ፣የወባ በሽታ ቅኝት፤ ክትትልና ግምገማን ማጠናከር ፣ምርመራና ህክምና መስጠት የወባ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ተግባራት ላይ በሚገባ ስራዎችን መሠራት እንደሚገባ ገልጸዋል ።
የዳውሮ ዞን ም/አስተዳዳሪ እና የገቢዎች መመሪያ ኃላፊ አቶ አሰፋው ደሣለኝ በበኩላቸው የወባ ወረርሽኝ ለመቆጣጠር የተጀመሩ ሥራዎችን ማጠናከር እና ሁሉም አካላት በትብብር በመሠራት እና ህብረተሰቡም የሚሰጣቸውን ትምህርት በአግባቡ ተግባራዊ በማድረግ ሊከላከሉ እንደሚገባ ገልጸዋል።
በአጠቃላይ በውይይት መድረኩ የወረዳው አመራር አካላት፣ የወ/ሃኔ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ፣ መምህራን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ዘገባው ገና ወረዳ መንግሰት ኮሙኒኬሽን ነው።