ለቴፒ ከተማ ጤና ባለሙያዎች እና ለጤና ጣቢያ ኃላፊዎች የልጅነት ልምሻ መከላከያ ክትባት ዘመቻ ስልጠና ሰጠ::

የሸካ ዞን ጤና መምሪያ ለቴፒ ከተማና ለየኪ ወረዳ ጤና ባለሙያዎች የፖሊዮ/የልጅነት ልምሻ/ መከላከያ ክትባት ዘመቻ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በቴፒ ከተማ ሰጥቷል።
በስልጠናው እድሜያቸው ከአምስት አመት በታች የሆኑ ህጻናት በአጠቃላይ በዘመቻ በተቀናጀ መልኩ ክትባት የሚሰጣቸው መሆኑ ተገልጿል።
ክትባቱ ከየካቲት 14 እስከ የካቲት 17 ለተከታታይ አራት ቀናት በቴፒ ከተማ እና በየኪ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ እድሜያቸው ከአምስት አመት በታች ለሆኑ ህጻናት እንደሚሰጥ ተገልጿል።
ህጻናት በወቅቱ የሚሰጡ የፖሊዮ መከላከያ ክትባትን ካላገኙ ለአካል ጉዳተኝነት የሚዳርግ በሽታ በመሆኑ ወላጆች ልጆቻቸውን በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ሊያስከትቡ ይገባል ተብሏል።
ህጻና ክትባቱን ከወሰዱ በኋላ ምናልባት ሊከሰቱ የሚችሉ ትኩሳት፣ መነጫነጭ፣ ማቅለሽለሽ፣ ማስመለስ፣ ተቅማጥ፣ ሽፍታ፣እና ሌሎች ምልክቶች ሊከሰቱ ስለሚችሉ ምልክቶቹ ከታዩ ክትባቱን ከተወሰዱበት ቀን እስከ 28ተኛው ቀናት ውስጥ እናቶች ለጤና ባለሙያዎች ሪፖርት ሊያደርጉ እንደሚገባ ተገልጿል።
አንዳንድ የጤና ባለሙያዎች በሰጡት አስተያየት ስልጠናው አስፈላጊ መሆኑን ተናግረው ወደ ስራ ሲገባ ያለው ጊዜ አጭር በመሆኑ የሙያ ስነ- ምግባርን በተከተለ መልኩ ሊተገበር ይገባል ሲሉ ሀሳባቸውን የሰጡ ሲሆን ከመድረክም ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል።
ስልጠናውን የሸካ ዞን ጤና መምሪያ እና የየኪ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ባለሙያዎች እና ሀላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
ዘገባው የየኪ ዘረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።