ለወባ ትንኝ መራቢያ ምቹ የሆኑ ስፍራዎችን የማፍሰስና የማዳፈን የመድኃኒትና የአጎበር ሥርጭት፣ እንዲሁም የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን በልዩ ትኩረት እየተሠራ እንዳለበት ተገለጸ።
የወባ በሽታ የእስካሁን አፈጻጸም ሪፖርት ቀርበው ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል።
ከአየር ንብረት ለውጥና ከህብረተሰቡ መዘናጋት ጋር ተያይዞ በወረዳው የወባ በሽታ ስርጭት ከፍተኛ እንደነበር ያስታወሱት የሎማ ቦሳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ኢንጅነር ዘለቀ ሲሳይ፤ የመድኃኒትና የአጎበር ሥርጭት፣ ለወባ ትንኝ መራቢያ ምቹ የሆኑ ስፍራዎችን የማፍሰስና የማዳፈን እንዲሁም የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን በልዩ ትኩረት እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡
ይህን የወባ ስርጭት መግታት የሚቻለው በተወሰነ አካላት ብቻ አይደለም ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል በማስተሳሰር፣ በመደጋገፍ እና በማስተባበር ለውጥ ለማምጣት እየተሰራ ነው ብለዋል። ብለዋል።
ኢንጅነር ዘለቀ አክለውም በተለይ በአሁኑ ሰዓት የፌዴራል፣ የክልልና የዞን መንግስት ወባ ለመከላከል ያላቋረጠ ድጋፍና ክትትል እያደረገ እንደሆነ በመጥቀስ ይህን ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
የዳውሮ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ባሹ መኮንን የወባ በሽታ ስርጭቱን ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት ህብረተሰቡ በአካባቢው ለወባ ትንኝ መራቢያነት አመቺ የሆኑ ውሃ ያቆሩ ስፍራዎችን በማፋሰስ፣ በማዳፈንና አጎበር በአግባቡ በመጠቀም ስርጭቱን እንዲቆጣጠር አሳስበዋል።
የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ ቴክኒካል አድቫይዘር የሆኑት አቶ ሰይፉ ባሻ በበኩላቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ወባን ለመቆጣጠር ብሎም ለማጥፋት እንዲሁም የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ በርካታ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል።
ወባ በአለም ገዳይ ከሆኑ በሽታዎች አንዱ መሆኑን ጠቁመው፣ በህብረተሰብ ላይ የከፋ ሞትና ጉዳት እንዳያስከትል በመከላከልና መቆጣጠር ሥራው ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መስራት እንዳለበት ገልጸዋል።
ከውይይቱ በኋላ ከፌዴራል ጤና ሚኒስቴር የመጡ ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን ቡድን፣ ከዞን ፐ/ሰ/ሰ ሀ/ል/መምሪያ ም/ኃላፊ አቶ ባሹ መኮንን፣ የወረዳው ዋና አስ/ሪ ኢ/ር ዘለቀ ሲሳይ፣ የወረዳው ጤና ጥበቃ ተወካይ አቶ ብርሃኑ ዶግሦና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ያሎ ጤና ጣቢያ በመገኘት የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ተመልክተዋል።
ዘገባው የሎማ ቦሳ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።