ማህበራዊ ብልጽግና በማረጋገጥ ሁሉም ዜጋ ጤናው የተጠበቀ እንዲሆን በትኩረት መሠራት እንዳለበት አቶ ኢብራሂም ተማም ገለፁ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም በታርጫ ከተማ ኢንላይት አካዳሚ ትምህርት ቤት ላይ ክልላዊ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ በይፋ አስጀምረዋል።
አቶ ኢብራህም ከ552ሺህ በላይ ህፃናትን በፖሊዩ ክትባት ዘመቻ እደሚሳተፉት በመግለጽ በክትባቱ ዘመቻ ሁሉም ህፃናት ማስከተብ የወላጅ ግዴታ ሲሆን የህፃናት መብትን በማስጠበቅ ሁሉም ዜጋ ኃላፊነት መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል።
በማስጀመሪያ በመርሃ ግብሩ የተገኙ የዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አሥራት ቸርነት የፖሊዮ በሽታ በሀገር ደረጃ ለማጥፋት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን በመግለጽ የተቀናጀ ሀገር አቀፍ ፖሊዮ ክትባት በዳውሮ ዞን ደረጃ ቤት ለቤት ከ116ሺህ በላይ ህፃናት እንደሚሰጥ ገልፀዋል።
በፓሊዮ ክትባት ማስጀመሪያ መራግብር ላይ አቶ ኢብራሂም ተማምን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ ባለሙያ፣ የዞን ጤና መምሪያ ኃላፊና ባለሙያ የዓለም ጤና ድርጅት እና ለሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።