በሆስፒታሎች የሚሰጡ አገልግሎትችን ምቹ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።

የታርጫ አጠቃላይ ሆስፒታል ክላስተር ”ሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት” 4ኛ ዙር ድጋፋዊ ክትትል ግብረ መልስ በታርጫ ከተማ ሰጥቷል።
የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ የህክምና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ገነት ደምሴ ሆስኘታሎችን በባለሙያና በግብዓት በማጠናከር ለተገልጋይ የሚሰጡ አገልግሎችን ጥራት ለማሻሻል እየተሰራ መሆኑ ገልጸዋል።
ሆስፒታሎች ያከናወኗቸውን ተግባራት በመረጃ በማስደገፍ መያዝ እንደማገባቸው ገልጸው ለቀጣይ መሰል ግምገማ የተሻለ ውጤት ይዘው መቅረብ ይገባል ብለዋል ወይዘሮ ገነት።
ዳይሬክተሯ አክለው በሆስፒታሎች የሚሰጡ የህክምና አገልግሎቶችን በጥራት ተደራሽ ለማድረግ ጠንክሮ በመስራት የኢትዮጵያ ”ሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት” 4ኛ ዙር ግምገማ ወቅት የተለዩ ችግሮች በአፋጣኝ ማረም ይገባል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ሆስፒታሎች ”ጥምረት ለጥራት” ግብረ መልስ ወቅት መልዕክ ያስተላለፉት የታርጫ ጠቅላላ ሆስፒታል ስራስኪያጅ አቶ ያዕቆብ ሌንጫ እንደገለጽት በታርጫ ጠቅላላ ሆስፒታል ፣ በገሣ እና ቶጫ የመጀመሪ ሆስፒታሎች የመመሰጡ አገልግሎት ለማሻሻል ሰፊ ጥረት ተደርጓል።
የሆስፒታሎችን አገልግሎት ለማሻሻል የሆስፒታል ስራ ኃላፊዎች ፣ የቦርድ አባላት እና የፓለቲካ አመራር አካላት በጋራ ቅንጅት መስራት ይጠበቃል ብለዋል።
በዚሁ ግብረ መልስ ወቅት እንደተገለጸው ውስን ሀብት በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ ያመለከቱ ሲሆን በተለይ ለእናቶች አገልግሎት ከመንግስት የተበረከቱ አንቡላንሶች ለታለመለት አለማ ብቻ መጠቀም ይገባል ብለዋል።
ከተሳታፊዎች አንድንዶቹ በሰጡት ሀሳብ የህብረተሰቡን ህክምና አገልግሎት ፍላጎት ለማሟላት አዳዲስ አሰራሮችን በመንደፍ ተጨባጭ ውጤት በሆስፒታሎቻችን ለማምጣት እንሰራለን ብለዋል።
በመድረኩ የታርጫ ጠቅላላ፣ የቶጫ ፣ አመያ እና የገሣ የመጀመሪያ ሆስፒታሎች አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ የልምድ ልውውጥ የተደረገ ሲሆን በመጨረሻም የሆስፒታል ስራ ኃላፊዎች የጋራ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመው ሰብሰባው ተጠናቋል።