በሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ጤና ጽህፈት ቤት በሚዛንና ጋቸብ ጤና ጣቢያዎቾ ወቅታዊ የህክምና አገልግሎት አሰጣጥን የተመለከተ የውይይት መድረክ ተካሄደ።

በውይይት መድረኩ የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ወንድሙ አይሳ፣ የተቋሙ የስራ ሂደት አስተባባሪዎች፣ የሁለቱ ጤና ጣቢያ አጠቃላይ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
ውይይቱ በሁለቱ ጤና ጣቢያዎች የተደረገውን የመስክ ስራ ተከትሎ የተከናወኑና ቀሪ ተግባራትን በመለዬት በቀጣይ በትኩረት የሚሰሩ ስራዎች ላይ ተወያይቶ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተጠቅሷል።
በሁለቱ ጤና ጣቢያዎች የሚሰጠው የህክምና አገልግሎት፣ የግብአት አጠቃቀም፣ የባለሙያ የመንግስት የስራ ሰአት አከባበር፣ የስራ ክፍሎች ተቀናጅተው መስራት ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በመለዬት በቀጣሪ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ዙሪያ ያተኮረ መሆኑም ተጠቅሷል ሲል የዘገበው የሚዛን አማን መንግስት ኮሙኒክሽን ጉዳየች ጽ/ቤት ነው።