በምዕራብ ኦሞ ዞን በክረምት በጎ ፍቃድ ሥራዎች አንዱ የሆነ የደም ልገሳ ፕሮግራም በጀሙ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።
በፕሮግራሙ የዞኑ የፖለቲካ እና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ሃላፊ አቶ አቤል ኢሳያስ እንደተናገሩት በዞኑ የደም ልገሳ
ፕሮግራም ከዚህ በፊት በባቹማ ከተማ መካሄድ አውስተው በዞኑ ከ260 እስከ 360 ዩኒት ደም ለመሰብሰብ እየተሰራ መሆን እና በባቹማ ከተማ በነበረው ልገሳ ከ87 የኒት በላይ የደም መሰብሰብ መቻሉን ገልጸዋል።
ደም መሰጠት ደንበር አይገዲብም ያሉት አቶ አቤል
በሄዳችሁበት አካባቢ ሁሉ ደም በመለገስ ክብር የሆኑ የሰው ልጅ ህይወት መታደግ አለብን ብልዋል።
አያይዘውም ሁሉም አመራሮች ፣ የመንግስት ሰራተኞች የከተማ ነዋሪዎች በዚህ ሥራ የተለመደው ግንባር ቀደምትነት ማሳየት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የዞኑ ጤና መምሪያ ሃላፊ አቶ ሼማጂ ጉሪጩማ በበኩላቸው በየሆስፒታሎች እና በጤና ጣቢያዎች ክብር የሆነ የሰው ልጅ ህይወት በደም እጦት ምክንያት እየተቸገሩ በመሆኑ ሁሉም አካላት የበኩላቸውን ሚና መወጣት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
በከተማ ያሉት ዕድሜያቸው ከ18 በላይ የሆነ አካላት ሁሉ የጤንነት ምርመራ በማድረግ ደም በመለገስ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
የጀሙ ከተማ ከንቲባ አቶ ወንድራድ ፋጅዮ እንደተናገሩት በክረምት በጎ ፍቃድ ሥራዎች በከተማ በርካታ ውጤታማ ሥራዎች እየተሰራ መሆኑ ጠቅሶ ህይወት ለማዳን ደም መለገስ አለብን ነው ያሉት።
በፕሮግራሙ የተገኘው የዞን እና የከተማው ከፍተኛ የሥራ አመራሮች ደም በመለገስ ፕሮግራም ያስጀመሩ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት በጀሙ ከተማ እንደሚካሄድ ተገልጿል።
ዘገባው የምዕራብ ኦሞ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።