በምዕራብ ኦሞ ዞን የወቅታዊ የጤና ሥራዎች ዙሪያ ዉይይት ተደርጓል።

በምዕራብ ኦሞ ዞን የክልሉ ጤና ቢሮ አመራሮች ከዞኑ አመራሮች ጋር በመሆኑ የወቅታዊ የወባ እና ሌሎች ሥራዎች ዙሪያ ዉይይት እና ግምገማ አድርጓል።
በዉይይቱ በ3 ወራት ዉስጥ 73ሺህ 352 የህብረተሰብ ክፍሎች ተመርምረው 49ሺህ 335 በላይ አካላት በወባ መያዛቸውን ጠቅሶ የወባ ምጣኔ 67%ላይ መሆኑ ገልጸዋል።
የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ በድሉ መዓዛ በበኩላቸው እንደተናገሩት የጤና ሥራዎች ህይወት የማዳን ጉዳይ በመሆኑ በቅንጅት መምራት ይጠበቃል ብልዋል።
በባለፈው የዘመቻ ወቅት የተደረገው የቤት ለቤት እንዲሁም በየጤና ኬላዎች ያሉት የህክምና አገልግሎቶች ዉጤት መኖሩን አውስተዋል።
የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ሃይሌ እንደተናገሩት የወባ መከላከል እና መቆጣጠር ላይ በትኩረት መስራት ይጠበቃል ነው ያሉት።
መደበኛ የጤና ሥራዎች የእናቶች ሞት ለመቀነስ የእናቶች ማቆያ ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል።
በዛሬው የተጀመረው የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ክትባት በልዩ ከ9 እስከ 14 እድሜ ያላቸው ልጆች እንድከተቡ ክትትል ማድረግ ይጠበቃል ብልዋል።
ጽዱ የጤና ተቋማት ከመፍጠር አንጻር ልዩ ትኩረት ተሰጠው መስራት እንደሚገባ ተናግሯል።
አያይዘውም የእናቶች ሞት አንዱ እና ዋንኛው የደም እጥረት በመሆኑ በዚህ ዘመቻ የደም መሰብሰብ ሥራ በትኩረት እንደሚሰራ አቶ ሃይሌ አክሎበታል።
የዞኑ ጤና መምሪያ ሃላፊ አቶ ሼማጂ ጉሪጩማ እንደገለፁት በባለፉት ጊዜት በተሰራው የዘመቻ ሥራዎች ዉጤት መታየቱ ገልጾ ሥራዎች ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል።
አክለው ወባን ለመከላከል ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑ ጠቅሶ ከ74ሺህ 395 ቤቶች በዚህ በ3ወራት ዉስጥ ጉብኝት ተደርጎ ከ37ሺህ 717 ቤቶች አጎበር በአግባቡ እየተጠቀሙ መሆናቸው ተናግሯል።
በ3ወራት ዉስጥ ከ371ሺህ 839 ካሬሜትር ቦታ በጊዜያዊ እና በቋሚ ተለይቶ 369ሺህ 240 ካሬ ሜትር ላይ የማዳፈን እና የማፍሰስ ሥራዎች መሰራቱን ተገልጿል።
የወባ መመርመሪያ መሳሪያዎች እና መድኃኒቶች በየጤና ኬላዎች ቀርበው የህክምና አገልግሎት እየተሰጣቸው መሆኑ ተናግሯል።
የጤና የዘመቻ ሥራዎች ለተከታታይ ሁለት ወራት በሁሉም ወረዳ እና ከተሞች እንደሚደረግ አስታውቋል።
ዘገባው የምዕራብ ኦሞ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።