በሺሾ እንዴ ወረዳ በዛሬው ዕለት 30 በጎ ፈቃደኞች ለቦንጋ ቅርንጫፍ ደም ባንክ ደም መለገሳቸዉ ተገለፀ ።

በሺሾ እንዴ ወረዳ በዛሬው ዕለት 30 በጎ ፈቃደኞች ለቦንጋ ቅርንጫፍ ደም ባንክ ደም መለገሳቸዉ ተገለፀ ።

የሺሾ እንዴ ወረዳ ሴ/ህ/ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ባንቻዬሁ ወዲሞ እንዳሉት ደም በመለገስ ህይወትን ያድኑ በሚል የወረዳ አመራሮችንና ሠራተኞችን በማስተባበር በፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ደም መለገሱን ገልፀዋል።
የጽ/ቤቱ ኃላፊ እንዳሉት በሺሾ እንዴ ወረዳ በዕለቱ በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ የደም ልገሳ ሲከናወን ውሏል ብለዋል። በውሎው በተደረገው የደም ልገሣ 30 በጎ ፈቃደኛዎች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 3ቱ ሴቶች ናቸው።
በዕለቱም ከቦንጋ ቅርንጫፍ የደም ባንክ የመጡ ባለሙያዎች አስፈላጊውን ቅድመ ምርመራ በማድረግ የደም ልገሳ ሂደቱን ያከናወኑ ሲሆን የወረዳው የመንግሥት ሠራተኞችና አመራሮች ባጭር ጊዜ ውስጥ ለወገን አለኝታነቱን ያሳየበት ዕለት መሆኑን ጠቅሰው አድናቆታቸውን ገልፀዋል።
የዘገበው የሺሾ እንዴ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳይ ጽ/ቤት ነው!