በባለፉት ወቅት የገጠሙን የኩፍኝ ወረርሽኝ እና የወባ ወረርሽኝ እንዳይደገም መከላከል ላይ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ተገለጸ።

በምዕራብ ኦሞ ዞን የዞኑ ጤና መምሪያ የ3ዓመት የልማት እና ኢንቨስትመንት እቅድ የተቋሙ የ2016 አፈጻጸም እና የኤችአይቪ ኤድስ እስትራቴጂ እቅድ የ2017 እቅድ ላይ የምክክር መድረክ ተካሂዷል።
በመድረኩ የምዕራብ ኦሞ ዞን ጤና መምሪያ ሃላፊ አቶ ሼማጂ ጉሪጩማ እንደተናገሩት ወረርሽኝ የመከላከል ሥራዎች ላይ ልዩ ትኩረት መስጠት ይጠበቃል ብልዋል።
በባለፈው በጀት አመት ከ11ሺህ 228 ሰው ተመርምረው 98 አካላት ላይ በደማቸው ኤችአይቪ ኤድስ መገኘቱ ገልጸዋል።
በአሁኑ ሰዓት ህብረተሰቡ እየተዘነጉ ያለው በሽታ በመሆኑ የመከላከል ሥራ እና ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቃል ያሉት ሀላፊው በዞኑ 1ሺህ 592 የሴቶች ልማት ህብረት መደራጀቱ ተጠቅሶ ከተደራጁት ዉስጥ 87%ምዘና መደረጉ ተገልጿል።
የማህበረሰብ አስተያየት መስጫ ካርድ አፈጻጸም 57% ላይ በመሆኑ ይህ የመልካም አስተዳደር ችግሮች መለያ አንዱ መንገድ በመሆኑ በየደረጃው ያሉት አካላት ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ተጠቅሷል።
በተጠናቀቀው በጀት አመት የግል ክሊኒኮች ሱፐርቪዥን ተደርጎ 34 የጤና ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰድ መቻላቸውን አስታውቋል።
አያይዘውም የወባ ወረርሽኝ የዘመቻ ሥራ ከተጠናከረ እና የምርመራ እና የህክምና አገልግሎት በየጤና ኬላዎች ሥራዎች ከተጀመረ በኃላ ለዉጥ መታየቱ አክሎበታል።
የወባ ወረርሽኝ ለመከላከል በዞኑ ቋሚ እና ጊዛዊ የወባ መራቢያ ከ56ሺህ,811በላይ ካሬ ሜትር ተለይተው ከ54ሺህ 212 ካሬ ሜትር በላይ የማፍሰስ እና የማዳፈን ሥራዎች መሰራቱን ተገልጿል።
በተደረገው 68ሺህ 197 የቤት ለቤት ጉብኝት ላይ 33ሺህ 782 አባወራዎች በአግባቡ አጎበር እየተጠቀሙ መሆናቸው ተመልክቷል።
የዞኑ የአደረጃጀት ዘርፍ ምክትል ሃላፊ አቶ ስንታየሁ ገሰሰን በበኩላቸው በየጊዜው እየተከሰቱ ያሉት ወረርሽን ጠንካራ የሆነ አደረጃጀት በመፈጠር መስራት ይጠበቃል ብልዋል።
ህብረተሰቡ የወረርሽኝ መከላከል ሥራዎች ላይ ልዩ ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ዘገባው የምዕራብ ኦሞ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።