በከጪ ወረዳ የወባ ወረርሽኝ መከላከል ስራዎች አፈፃፀም ሪፖርት እና የክትባት ማካካሻ (RED /REC MP Development With actual Head Count) የኦረንቴሽን መድረክ ተካሂዷል ።
የስልጠናውን ሰነድ ያቀረቡት የከጪ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት እናቶችና ህፃናት ስራ ሂደት አስተባባሪ ወ/ሮ ናርዶስ ኃ/ማሪያም የክትባት ማካካሻ ሰነዱን በማቅረብ ሰፊ ማብራሪያ ስጥተዋል ።
የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብዙአየሁ ዘርሁን በበኩላቸው በወረዳችን ያለው የሆነ የወባ ስርጭት የመከላከል እና የመቆጣጠር ስራ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በመረባረብ የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገባችን የሚታወቅ ቢሆንም ምንም ክትባት ያልተከተቡ እና ክትባት ጀምረው ያቋረጡ ህፃናትን መከተብ እና ቤት ለቤት ቆጠራ መሰራት አለበት ብለዋል።
በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ዉለታው ሁሴን የወባ ወረርሽኝ ከሃገራችን አልፎ መላው አህጉራችን ላይ ገዳይ ከሚባለው በሽታዎች ከፍተኛ ቁጥር የያዘው በሽታ ቢሆንም በዘንድሮው ዓመት በወረዳችን የተሰሩ የመከላከል እና የመቆጣጠር ስራ ከፍተኛ ነው ስሉ ተናግረዋል ።
አክለውም በወረዳው በአምስቱ ቀበሌዎች እየተስተዋለ ያለ የወባ ስርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ከወረዳው አመራር፣ ደጋፊ ባለሙያዎች ፣ ጤና ኤክስቴንሽኖች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ባለፉት ወራት ርብርብ ማድረጋቸው ጠቅሰው ለወደፊቱም የአከባቢ ንፅህና በመጠበቅ እና ለማህበረሰቡ ግንዛቤ በመስጠት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩሉን ኃላፊነት መወጣት አለበት ስሉ ገልፀዋል ።
በመድረኩም የወረዳው አስተዳደሪ፣ የጤና ባለሙያዎች፣ ጤና ኤክስቴንሽኖች እና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል ።
ዘገባው የከጪ ወረዳ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።