በካፋ ዞን አዉራዳ ከተማ አስተዳደር የማዐጤመ አገልግሎት ብዙ ወጭ አውጥተው ከመታከም እንዳዳናቸው የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ገለፁ ።
የማህበረሰብ ዐቀፍ ጤና መድህን የአገልግሎት ተጠቃሚ ከሆኑት አንዳንዶች እንደገለጹት ውስን ገንዘብ በመክፈል መላው የቤተሰብ አባላት የጤና አገልግሎት የመጠቀማቸውን አብራርተዋል።
የማአጤመ አባል ከሆኑ በሪፈር ወደሌሎች ሆስፒታሎች በመሄድ የህክምና አገልግሎት መጠቀም እንደሚችሉ አስተያየት ሰጭዎቹ ገልጸዋልል።
አልፎ አልፎ በአንዳንድ የህክምና ተቋማት የሚስተዋሉ ችግሮች በሂደት እየተቀረፈ መሆኑን ገልጸው አገልግሎቱ የበለጠ እንዲሳለጥ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ጠይቀዋል።
በመጨረሻም የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል አባል በመሆን መንግስት የሰጠውን በጎ ዕድል እንዲጠቀሙ ጠይቀዋል ሲል የዘገበው የአውራዳ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ነው።