በካፋ ዞን ዋቻ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በማህብረሰብ ተሳትፎ በተደረገው ገንዘብ ድጋፍ የ”CBC” ማሽን ተገዝቶ አገ/ት መስጠት ጀመረ

በማህብረሰብ ተሳትፎ በተደረገው ገንዘብ ድጋፍ ከ20 በላይ የደም ዓይነቶችን በአንዴ ምርመራ ማድረግ የሚችል “CBC” hematology ማሽን በ530 ሺህ ብር ተገዝቶ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የዋቻ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አስታውቋል።
ማሽኑ በማህብረሰብ ተሳትፎ የተገዛ ሲሆን የሆስፒታሉን የውስጥ አገልግሎት አሰጣጥ ደረጃውን ለማሻሻል እየተደረገ ያለው ጥሬት ላይ ድርሻው የጎላ መሆኑ ታምኖበታል።
አሁንም የማህብረሰብ ተሳፎዎችን በማጠናከር ሌሎች አስፈላጊ ግብዓቶችን በማሟላት ለማብረሰቡ አስፈላጊ አገልግሎቶችን ለመስጠት በትኩረት እየተሠራ ይገኛል ያሉት የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ተረፈ አዴሎ ናቸው።
ቀጣይ የፅኑ ህክምና ማዕከል፣የማህብረሰብ ፓርማሲ፣ የሠራተኞች መኖሪያ ቤት ግንባታ እና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ለማሟላት በከተማ አስተዳደሩና በወረዳው የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ማህብረሰቡን እያስተባበሩ መሆናቸውን አክሏል።
የተገዛው ማሽን የታካሚዎችን በትንሽ ገንዘብ አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ ያሉት ሥራ አስኪያጁ ቀጣይ የተጀመሩ ድጋፎች ተጠናክሮ እንዲቀጥሉም ጠይቋል።
በመጨረሻም ድጋፍ ያደረጉ የማህብረሰብብ ክፍሎችንና እያስተባበሩ ያሉትን አካላት አመስግኗል።
ዘገባው የጨና ወረዳ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ነው