በክልሉ በጤና አገለግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ከህብረተሰብ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት በልዩ ትኩረት ይሰራል_ ጤና ቢሮ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ
በ2017 በተለዩ በዋና ዋና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።
በመድረኩ የተገኙ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም በክልሉ በጤና አገለግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ከተገልጋይ ህብረተሰብ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት በልዩ ትኩረት ይሰራል እንደሚሰራ ገልጸዋል።
የመልካም አስተዳደር ችግሮች ከግል ስነ ምግባር ጋር የሚገናኝ መሆኑን የገለፁ አቶ ኢብራሂም ተማም በጤና ዘርፍ ያለ ሁሉም ፈፃሚና አስፈፃሚ መልካም ስነምግባር በማጎልበት ለማህበረሰቡ ተገቢውን አገለግሎት መስጠት እንደሚገባ አሳስበዋል።
በቢሮው የተዘጋጀውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች መፍቻ ዕቅዶቻችን ወደ ተጨባጭ ተግባር በመቀየር ለማህበረሰብ ተጠቃሚነት ቅድሚያ ተሰጥቶ ልሰራ ይገባል ያሉት የቢሮው ሀላፊ በጤና ተቋም የሚገኝ ሁሉም የባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን ሀላፊነት በተገቢው ልወጡ እንደሚገባም አስረድተዋል።
የቢሮው ምክትል ሀላፊና የህክምና አገለግሎቶች ዘርፍ ሀላፊ አቶ ምትኩ ታመነ በበኩላቸው በተለይ በታችኛው የአስተዳደር መዋቅሮች የወቅቱን የመድኃኒት ዋጋ እና የተገልጋይ ህብረተሰብን ፍላጎትን መሠረት ያደረገ የመድኃኒት ግዥ በጀት ልመደብ እንደሚገባ አስረድተዋል።
ከጤና ባለሙያዎች ቅጥር፣ ምደባ፣ ዝውውር ና የትርፍ ሰዓት ክፍያ ጋር በተያያዘ በታችኛው መዋቅር የሚታዩ ክፍተቶች ልታረሙ የሚገቡ መሆኑም በአፅንኦት ተነስቷል።
ለማህበረሰብ ዐቀፍ ጤና መደህን አገለግሎት ከተገልጋይ ማህበረሰብ የሚሰበሰብ ገንዘብ በወቅቱና በትክክል ለተባለለት አላማ ማዋል የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ስለሆነ ለዘርፉ ትኩረት ልሰጥ ይገባልም ብለዋል።
ጠንካራ የቁጥጥርና የክትትል ስርዓት በመዘርጋትና የውስጥ አቅም በማሳደግ ለህብረተሰቡ ተገቢ የጤና አገለግሎት ለመስጠት ይሰራል ተብሏል።
በክልሉ ተጀምሮ ያልተጠናቀቁ የጤና ተቋማት ግንባታዎች ተጠናቅቀው ለህብረተሰብ አገለግሎት እንዲበቁ የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተብራርቷል።
በመድረኩ በቁጥጥርና ክትትል ስራዎች ላይ ህብረተሰቡን በስፋት በማሳተፍ ውጤት ማምጣት እንደሚቻልም የተጠቆመ ስሆን በክልሉ ከጤና አገለግሎት አሰጣጥ ጋር በህብረተሰቡ ዘንድ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በዝርዝር በዞን ጤና መምርያ ኃላፊዎች፣ በክልል ጤና ቢሮ አመራሮችና አጠቃላይ ሰራተኞች ቀርበው ችግሮቹ መፈታት የሚችሉበት ቀጣይ አቅጣጫ ተቀምጧል።