በክልላችን 157 ሺህ 230 ልጃገረዶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የማህጸን በር ጫፍ ካንስር መከላከያ ክትባት እንደሚሰጥ ጤና ቢሮ አስታወቀ
ጥናቶች እንደሚያሳዩት በአገራችን ኢትዮጵያ በማህጸን በር ጫፍ ካንስር በሽታ በአማከይ 7 ሺህ 4 መቶ 45 ሴቶች በበሽታዉ እንደሚያዙና 5 ሺህ 3 መቶ 35 ሴቶች እንደሚሞቱ የጥናት ሪፖርቶች ያሳያሉ፡፡
በዓለም እንዲሁም በአገር ደረጃ የስርጭት አድማሱ እያሰፋ የመጣዉን የማህጸን በር ጫፍ ካንስር በሽታ ጫና ለመቀነስ የክትባት ዘመቻ ከህዳር 09-142017 ዓ.ም በአገር አቀፍ እንዲሁም በክልል በሁሉም ዞኖች ዘመቻዉ እንደሚካሄድ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም አስታዉቀዋል፡፡
በዘመቻዉ በሁሉም የክልላችን ዉስጥ የሚገኙ ዕድሜያቸዉ ከ9-14 ዓመት ያሉ ልጃገረዶች ክትባቱን እንደሚወስዱና በየደረጃው ያሉ አመራሮቻችን፣ የጤና ባለሙያዎች፣ መምህራኖች፣ የሴቶች አደረጃጀቶች ፣ የሀይማኖት አባቶች እና የሃገር ሽማግሌዎች ለዘመቻዉ ዉጤታማነት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡
ዘመቻዉን ዉጤታማ ለማድረግ ይረዳ ዘንድ የክልል ጤና ቢሮ ከቀበሌና ከትምህርት ቤት ጀምሮ የመለየትና ክትባቱን ተደራሽ ለማድረግ አስፈላጊዉን ስራዎች ሲከናወኑ የቆየ መሆኑን የቢሮዉ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም አስገንዝበዋል፡፡
በክልል ደረጃ 157 ሺህ 230 ልጃገረዶች ክትባቱን እንደሚወስዱና ከዚህ ዉስጥ138 ሺህ 421 በትምህርት ቤቶች ዉስጥ የሚከተቡ ሲሆን ቀሪዎቹ 18 ሺህ 8 መቶ 9 የሚሆኑት በጤና ተቋማትና በክትባት ጣቢያዎች እንደሚወስዱ የቢሮዉ ኃላፊ አሳስብዋል፡፡
ክትባቱ የሚሰጥባቸዉ ቦታዎች በትምህርት ቤቶች፣
በጤና ተቋማት እና በክትባት ጣቢያዎች መሆኑ ታዉቆ በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች ያሉ ልጃገረዶች ክትባቱን እንዲወስዱና በሀገር ደረጃ ጫና እያደረሰ ያለዉን የማህጸን በር ካንስር በጋራ እንከላከል ስሉ ኃላፊዉ ጥሪ አስተላልፈዋል።በዘመቻዉ ክትባቱን ከመስጠት በተጨማሪ ስለበሽታዉ አስከፊነት ህብረተሰቡን የማስተማር ስር በትኩረት ይሰራል ብለዋል አቶ ኢብራሂም፡፡