በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የጤና ምርመራና ህክምና አገልግሎት መጀመሩን ተገለጸ።
በካፋ ዞን የሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር ዩኒት የ2016 /2017 ዓ.ም ክረምት የበጎ ፍቃድ የጤና ምርመራና ህክምና አገልግሎት መሰጠት ተጀምሯል ።
የበጎ ፍቃድ አገልገሎት ሰጪ የህክምና ባለሙያዎች መዘጋጀታቸውን የገለፁት የሺሺንዳ ከተማ ማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ብርሃኑ ሀይለየሱስ ይህን እድል ህ/ሰቡ ተጠቃሚ በመሆን ያለምንም ወጪ በመመርመር የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አሳስቧል ።
በዘንድሮው በጎ ፍቃድ ምርመራና ህክምና አገልግሎት የደም ግፊት ፣የኤች አይቪ ኤድስ ፣የወባ ፣የስኳር ህመምን ጨምሮ ሌሎች ምልክት ሳያሳዩ ለሞት የሚያደርጉ በሽታ አይነቶች ነፃ የምርመራ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል።
”ሙያዬን ለሀገሬ” በሚል መሪ ቃል የዘንድሮው በጎ ፍቃድ የጤና ምርመራና ህክምና አገልግሎት ከነሀሴ 13/2016 ዓ.ም እስከ መስከረም 8/2017 ዓ.ም ለ 1 ወር ብቻ የሚቆይ አንደሆነ ገልጸዋል።
ህብረተሰቡ በሺሺንዳ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ በመምጣት በበጎ ፍቃደኝነት ለመመርመር ለሚፈልጉ በተዘጋጀው መመርመሪያ ክፍል በመገኘት በነፃ በመመርመር የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በመርሃ ግብሩ ተገልጿል ።
ዘገባው የሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዩኒት ነው።

