በወባ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ዘርፍ የተሰሩ ሥራዎች አፈጻጸምና የክትባት ማካካሻ ኦረንተሽን ውይይት መድረክ አካሄደ።
የዳውሮ ዞን ማሪ ማንሳ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት የወባ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ዘርፍ የተከናወኑ ሥራዎች አፈጻጸምና የክትባት ማካካሻ ኦረንተሽን መድረክ የተለያዩ የባለድርሻ አካላት በተገኙበት አካሂዷል።
በመድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የወረደው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተካልኝ በቀለ ወባ በአሁኑ ጊዜ በዓለም ደረጃ አሳሳቢ ከሚባሉ በሽታ አንዱ እንደሆነ ገልጸው እንደ ወረዳችን በአብዛኛው ቀበሌዎች እየተስተዋለ ያለውን የወባ ወረርሽን ለማጥፋት እየተደረገ ያለው ርብርብ የሚበረታታ እንደሆነ ገልጸዋል።
አክለውም በወረዳው እየተስተዋለ ያለውን ከፍተኛ የወባ ስርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ባለድርሻ አካላቱ በቀበሌ የሚገኘውን ማህበረሰብ ክፍሎችን በማስተባበር ግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት በመስጠት እና ግንዛቤ በመፍጠር በትኩረት መሠራት ይጨበቅባቸዋል ብለዋል።
የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በረከት ባቡሎ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ የወባ አስከፊነቱን በወል በመረዳት መከላከል ላይ ትኩረት በመስጠት አልጋ አጎበርን በአግባቡ በመጠቀም ከበሽታ ተጠቂነት ራሱን ማዳን እንደማቻል ገልጸዋል።
ክትባት ያልጀመሩ እና ጀምረው ያቋረጡ ህፃናት ለተከታታይ ቀናት በሚቆየው የማካካሻና የተደራሽነት የክትባት ዘመቻ መሰጠት እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡
በዚህ የክትባት ዘመቻ እድሜያቸው ከ1ዓመት በላይ እና ከ5 አመት በታች የሆኑ ምንም ክትባት ያልጀመሩ እና ክትባት ጀምረዉ ያቋረጡ ህፃናትን በማስከተብ ወላጆችና አሳዳጊዎች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርበዋል።
በመድረኩ ላይ ዋና አስተዳደርን ጨምሮ የፓርቲ አመራር፣ የሁሉም ቀበሌ ጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች፣ የጽ/ቤቱ ማናጅመንት አባላት እና ለሎች ተሳትፈዋል ።
ዘገባው የወረዳው መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው ።