በወባ ወረርሽኝ መከላከል ሥራ እየተመዘገቡ ያሉ አበረታች ወጤቶች ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁሉም መረባረብ እንደሚገባ ተጠቆመ።
የማሻ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የወባ ወረርሽኝ መከላከል ሥራ የ100 ቀናት ተግባራት ሪፖርት ግምገማ አካሂዷል።
ሪፖርቱን ያቀረቡት የማሻ ከተማ የበሽታ መከላከልና ጤና ማጎልበት ሥራ ሂደት አስተባባሪ ወ/ሮ ትዕግስት አየለ በከተማዋ የወባ ወረርሽኝ ህብረተሰቡን እንዳያጠቃ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ በመፍጠር ዘርፈ ብዙ ሥራዎች መሰራቱንና በተደረገው ርብርብ በወረርሽኙ ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን መቀነስ መቻሉን ገልፀዋል።
ባለፉት 100 ቀናት ወስጥ በከተማችን 3600 ሰዎች ላይ የወባ ምርመራ ተደርጎ 862ቱ ላይ በሽታው የተገኘበት መሆኑንና
ወረርሽኙ በተከሰተበት ወቅት ለወባ ትንኝ መራቢያ ስጋት በሆኑት ቦታዎች በዘመቻ ህብረተሰቡን በማሳተፍ የማፋሰስና የማዳፈን ሥራ ተሰርቶ እንዲሁም ከአቅም በላይ በሆኑት ቦታዎች የወባ ከሚካል ርጭት ተከናውኗል።
የግምገማ መድረኩን የመሩት የማሻ ከተማ ብ/ፓ/ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መልካሙ እንደሻው ወረርሽኙ በከተማችን የከፋ አደጋ እንዳያደርስ በጤና ባለሙያዎችና በአመራሩ ቁርጠኝነት በተደረገው ርብርብ ህብረተሰቡን በማሳተፍ በተሰራው ሥራ አበርታች ወጤት መመዝገብ መቻሉን ተናግረው በቀጣይም ይህ ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁሉም በትኩረት መስጠት አለበት ብለዋል።
የማሻ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ክቡርሰው አለሙ በበኩላቸው የጤና ጉዳይ ሁሉንም የምመለከት ጉዳይ መሆኑን ጠቁመው አሁን ያለንበት ወቅት ለወባ ትንኝ መራቢያ ምቹ በመሆኑ የመከላከል ሥራው በተቀናጀና በተጠናከረ መልኩ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል።
በቀጣይ ላይ ውጤቶችን በየወቅቱ መገምገም ለወረርሽኝ ስጋት የሆኑ ቦታዎች የመለየት፣ የመከላከል ሥራ መስራትና ክትትል ማድረግ እንደምገባ በመጠቆም ህብረተሰቡም ከህክምና ይልቅ መከላከል ላይ ትኩረት መስጠት እንዲሁም የቆመ መኪና፣ የልብስ ማጠቢያ ጎማዎችና ውሃ ያቆሩ ቦታዎች ላይ ክትትል መደረግ እንዳለበት በግምገማ መድረኩ ተመላክቷል።
ዘገባው የማሻ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።