በደቡብ ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት የማህጸን በር ጫፍ ካንስር መከላከያ ክትባት በትምህርት ቤቶች ፣ በጤና ተቋማት እና ጊዚያዊ ክትባት መስጫ ቦታዎች በይፋ መሰጠት ተጀምሯል።

በክልሉ ዛሬ በተጀመረው የክትባት ዘመቻ ዕድሜአቸው ከ9-14 ዓመት ውስጥ ለሚገኙ ከ157 ሺህ 230 ልጃገረዶች መሰጠት መጀመሩ እ ታውቋል።
በዓለም እንዲሁም በአገር ደረጃ የስርጭት አድማሱን እያሰፋ የመጣዉን የማህጸን በር ጫፍ ካንስር በሽታ ለመቀነስ የክትባት ዘመቻ ከዛሬ ከህዳር 09-14 2017 ዓ.ም ጀምሮ በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች መሰጠት መጀመሩን የደ/ም/ኢ/ህ/ ክ/መ ጤና ቢሮ ኃላፊ ተወካይ እና ጤናና ጤና ነክ ግብዓት ቁጥጥር ባለስልጣን ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አሰፋ ገልጸዋል።
ለክትባት ዘመቻ በየደረጃው ያሉ አመራሮች፣ የጤና ባለሙያዎች፣ መምህራኖች፣ የሴቶች አደረጃጀቶች ፣ የሀይማኖት አባቶች እና የሃገር ሽማግሌዎች የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥራ አስተላልፈዋል አቶ ሙሉቀን።
በክልሉ 157 ሺህ 230 ልጃገረዶች ክትባቱን እንደሚወስዱና ከዚህ ዉስጥ138 ሺህ 421 በትምህርት ቤቶች ዉስጥ የሚከተቡ ሲሆን ቀሪዎቹ 18 ሺህ 8 መቶ 9 የሚሆኑት በጤና ተቋማትና በጊዚያዊ የክትባት መስጫ ጣቢያዎች እንደሚወስዱ አስታውቀዋል።
የፌደራል ጤና ሚኒስቴር የእናቶች፣ ህጻናት እና አፍላ ወጣቶች መሪ ስራ አስፈጻሚ የክትባት አገልግሎት ጉዳይ አማካሪ አቶ ተካልኝ ሞርካ መንግስት የማህጸን በር ካንሰር ለመከላከል ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በዛሬው ቀን በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች የክትባት ዘመቻ ማስጀመሩን ገልጸው በደቡብ ም/ኢ/ህ/ክ/ መንግስት የተጀመረውን የክትባት ዘመቻ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው እንደሚደግፉም ገልጸዋል።
የሄው ዘመቻ አካል በምዕራብ ኦሞ ዞን በጀሙ ከተማ በጀሙ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የክልሉ ጤና ቢሮ ም/ሀላፊ እና የኘሮግራሞች ዘርፊ አቶ ሀላፊ አቶ ሀይሌ ዘውዴ በተገኙበት መጀመሩን ከስፍራው የደረሰው መረጃ የሚያመላክት ሲሆን ክልል አቀፍና የዳውሮ ዞን ክትባት ዘመቻ ማስጀመሪያ ኘሮግራም የክልል ጤና ቢሮ አመራር እና ባለሙያዎች ፣ የፌደራል ጤና ማኒስቴር የክትባት አማካሪዎች እና የዳውሮ ዞን አመራር አካላትና ባለሙያዎች በተገኙበት በታርጫ ከተማ አድቬንቲስት አንደኛ ደሰጃ ትምህርት ቤት ተጀምሯል።
የዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ ሀላፊ አቶ አስራት ቸርነት በማስጀመሪያ ኘሮግራም ላይ ተገኝተው በዞኑ በሚደረገው ዘመቻ ዕድሜያቸው ከ9-14 ዓመት ውስጥ የሚገኙ 42,268 ልጃገረዶችን ለመተብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ለዘመቻው ስኬት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ አስተላልፈዋል።