በዳውሮ ዞን ከ1መቶ 20ሺ በላይ ህፃናት በተቀናጀ ሀገር አቀፍ የፖሊዮ በሽታ ለመከላከል ክትባት እንደምሰጥ የዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ።
የተቀናጀ ሀገር አቀፍ ፖሊዮ በሽታ ለመከላከል ክትባት ለመስጠት የአሰልጣኞች ስልጠና በታርጫ ከተማ ተካሂዷል።
የዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አስራት ቸርነት የፖሊዮ በሽታ በሀገር ደረጃ ለማጥፋት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን በመግለጽ የተቀናጀ ሀገር አቀፍ ፖሊዮ ክትባት ቤት ለቤት እንደሚሰጥም ገልጸዋል።
አቶ አስራት የጤና ባለሙያዎች ፣የሃይማኖት አባቶች እና ባለድርሻ አካላት እና በየደረጃዉ ያሉ የአመራርና ባለሙያ የክትባት ዘመቻዉ ዉጤታማ እንዲሆን የድርሻቸዉን እንዲወጣ አሳስበዋል።
የፖሊዮ በሽታ ለመከላከል ከ5 ዓመት በታች ያሉትን ህፃናት ቀደም ሲል ክትባት የወሰዱና ያልወሰዱ ጭምር በክትባቱ እንደምሳተፉ አቶ አስራት አስታውቀዋል።
ክትባቱ ከየካቲት 14 እስከ 17 የሚጀመር በመሆኑ የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝት እና ምላሽ ቡድን አስተባባሪ አቶ ወልደ በካሎ ገልጸዋል።
አቶ ወልደ ዘመቻዉን ገጠር እና ከተማ በጥራት ተደራሽ ለማድረግ በየደረጃዉ ያለዉን ባለሙያ ሚናው ቀላል እንዳልሆነ በመግለጽ የጤናዉ ሴክተር አመራርና ባለሙያ ይህ ዘመቻ በተያዘዉ ጊዜ ጥራቱን ጠብቆ እንደሚጠናቀቅ እና በትኩረት ሽፋን እንደምሰጥ አስረድተዋል።
በየቀኑ በገጠር 125 በከተማ 250 በላይ ህፃናትን ለማዳረስ በትኩረት በመሠራት የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ በአለም እንዲሁም በአገር አቀፍ ደረጃ ለማጥፋት ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መሠራት እንደምገባ አቶ ወልደ በካሎ አክለዋል።
ዘገባው የዳውሮ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።