በገና ወረዳ የወባ ወረርሽኝን ለመከላከል እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።

በገና ወረዳ የወባ ወረርሽኝን ለመከላከል እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።

በወልደሀኔ ከተማ የወባ መከላከል የንቅናቄ መድረክ በወባ መከላከል፣ መቆጣጠር ዙሪያ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እንዲሁም በቀጣይ መደረግ ስለሚገባቸው ጉዳዮች በዝርዝር ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርገዋል ።
በመድረኩ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የገና ወረዳ አስተዳደር ተወካይ አቶ ገዛኸኝ ገበየሁ ህብረተሰቡ የወባን በሽታ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የአጎበር አጠቃቀም፣የአካባቢ ንፅህና ቁጥጥር እና ሌሎች የመከላከያ ተግባራት ላይ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል ፡፡
የወባ ወረርሽኝ ለመከላከል ከሚሰሩ ስራዎች አንዱ አካል የሆነው የአጎበር መጠቀም ሲሆን የአልጋ አጎበር አጠቃቀምን ጨምሮ፤ ያቆሩ ዉኃዎችን በማፋሰስ እንዲሁም፤ የግል ንጽህና በመጠበቅና የወባ ትንኝ መራቢያ ቦታዎችን በማዳፈን የድርሻቸውን እንዲወጣ አቶ ገዛኸኝ አሳስበዋል፡፡
የወባ በሽታ በመግታት ዜጎች እንዳይሞቱ ለማድረግ ስርጭቱ የሚስተዋልባቸውን አካባቢዎች በመለየት መከላከልን መሠረት ያደረገ ጥንቃቄዎችን በማድረግ የወባ ጫናን በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ የሁሉም አካላት ድርሻ ልሆን እንደሚገባ የገና ወረዳ ም/ቤት ዋና አፌ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፋናዬ መንገሻ ገልጸዋል።
ከወባ ነፃ የሆኑ አካባቢዎችን ለመፍጠር የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመጠቀም እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በማጠናከር ርብርብ ማድረግ ያስፈልጋል ያሉት የገና ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ተወካይ አቶ አስራት አሰፋ በተለይ የአጎበር አጠቃቀም ላይ ምርጥ ተሞክሮ ያለባቸውን አካባቢዎች በመለየት ማስፋት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
የወባ ወረርሽኝ ለመቆጣጠር በርካታ ስራዎች እየተሰሩ የሚገኝ ሲሆን ከነዚህም ማህበረሰቡን ያሳተፈ የመከላከልና የመቆጣጠር ተግባራትን በወረዳው ስር በሚገኙ ቀበሌያት በተጠናከረ መልኩ እየተሰራ እንደሚጠኝ ተገልጿል።
የወረዳው ከፍተኛ አመራሮች የቀበሌ አመራሮች የአከባቢው ማህበረሰብ እንዲሁም የጤና ባለሞያዎች በመቀናጀት በየአከባቢው ለወባ ትንኝ መራቢያ አመቺ የሆኑ ቦታዎችን የማፋሰስ የማዳፈን እንዲሁም የአከባቢ ቁጥጥር ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸው የገለጹት የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ዘነበ በተለይ የማህበረሰቡ ተሳትፎ መነቃቃቶች የታዩበትና ተስፋ ሰጪ ነው ብለዋል።
በመድረኩ የወረዳው አመራር አካላት ፣ የዞን ጤና ደጋፊ ባለሙያ ፣ የቀበሌ አመራር ፣ የዕድር መሪዎች እና ሌሎች አካላት ተሳትፈዋል ።
ዘገባዎ ገና ወረዳ መ/ኮሚኒኬሽን ።