በጤናው ዘርፍ እያደገ የመጣዉን የማህበረሰቡን ግንዛቤና ተሳትፎ ባህል በማድረግ የጤና ትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎችን በዘላቂነት ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ ::

ጽ/ቤቱ በዛሬዉ ዕለት የጤና ትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎችን በስኬት ያጠናቀቀዉን የገራ ቀበሌን በሞዴልነት አስመርቋል።
በምረቃ ፕሮግራሙ የተገኙት የጠሎ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አትርሴ ሻታቸዉ እንደተናገሩት የጠሎ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት በወረዳ ደረጃ ስለ ግልና አከባቢ ንፅህና አጠባበቅ የህብረተሰቡን ግንዛቤ፣ ዕውቀትና ክህሎት ከፍ በማድረግ አጠቃላይ የጤና ትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎችን ለማሳካት አበረታች ስራዎችን እየሰራ ነው።
በጤና ትራንስፎርሜሽን ስራዎች ሞዴል ከሆኑ ቀበሌዎች እስካሁን ስምንተኛ ቀበሌ እያስመረቁ መሆናቸዉን የገለጹት አስተዳዳሪው ጤናዉ የተጠበቀ ማህበረሰብ በአላማ የሚቀሳቀቀስ በመሆኑ በሁሉም መስክ ስኬታማ ናቸዉ ሲሉ አብራርቷል።
አቶ አትርሴ ማህበረሰቡ ስለ ንፅህና አጠባበቅ የያዘው ግንዛቤ ከግልና አከባቢ ንፅህና አጠባበቅ ጉድለት ከሚመጡ ተላላፊ በሽታዎች ለመጠበቅ ያግዛል ብሏል።
የካፋ ዞን ጤና መምሪያ ሃላፊ አቶ አክሊሉ አሰፋ በበኩላቸው አከባቢዉን በጤና ልማት ለማሻገር የሚታየዉ የህብረተሰብ ተሳትፎ የሚመሰገን በመሆኑ ለዘርፉ አካላት መነቃቃትን ይፈጥራል ብሏል።
አቶ አክሊሉ አክለዉም እያደገ የመጣዉን የማህበረሰቡን ግንዛቤና ተሳትፎ ባህል በማድረግ የጤና ትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎችን በዘላቂነት ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል።
በስተመጨረሻም የገራ ቀበሌ ንፅህና አጠባበቅ መሻሻልን የሚያመላክት ነጭ ባንዴራ የተሰቀለ ሲሆን ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት ምረቃ እንዲሳካ አስተዋጽኦ ላደረጉ የሴቶች ልማት ህብረትና ሌሎች አመራር አካላቶች የምስጋናና እዉቅና ሰርቲፍኬት ሰጥቷል።
ዘገባው የጠሎ ወረዳ መንግስት ኳሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።