በጤናው ዘርፍ ፈጣን የመረጃ ቅብብሎሽ ስርዓትን ለመፍጠር ዲጂታላይዝ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።
የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ መረጃን ዲጂታላይዝ ማድረግ በሚቻልበት ዙሪያ ላይ ውይይት አካሂዷል።
ደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ የኃላፊ ተወካይ እና ጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶች ግብአት ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣና ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አሰፋ መረጃ ዲጂታላይዝ አድርጎ መጠቀም የጤና አገልግሎት ስርዓትን ፈጣን በማድረግ ወቅታዊ ምላሽ እንዲሰጥ የሚያደርግ በመሆኑ የጤና ተቋማት ወደ ዲጂታል የመረጃ ስርዓት መግባት ግድ ይላል ብለዋል።
በመሆኑም ከጤና ኬላ ጀምሮ የሚሰነዱ መረጃዎች ለጤና አገልግሎት መሠረት በመሆናቸው ወቅቱን የሚመጥን የኤሌክትሮኒክስ መረጃ ስርዓትን ማጠናከር አግባብነትን በመገንዘብ ሁላችንም ለተግባራዋነቱ የበኩላችን ሚና መወጣት አለብን ብለዋል አቶ ሙሉቀን።
መረጃን ዲጅታል አድርጎ መጠቀም ለመረጃ ጥራትና ፍጥነት ከሚሰጠው ጥቅም ባሻገር ጊዜንና ገንዘብን በመቆጠብ የሀብት ብክነትን ያስቀራል፤ የቴክኖሎጂ ሽግግር በመፍጠር በዕውቀት የተካነ የሰው ኃይል እንዳፈጠርም ያደርጋል ብለዋል።
አቶ ሙሉቀን አያይዘው የአየር ንብረት ለውጥ የተፈጦሮ አየር ሚዛን መዛባት ተከትሎ በኮማንድ ፖስት አየተመራ የሚገኘው የወባ ወረርሽኝ በሽታ ላይ የሚዘጋጁ መረጃዎች ከምን ጊዜውም ይልቅ ፈጣን ለማድረግ ዲጂታል የመረጃ አያያዝን በማሳደግ ህብረተሰቡን የመታደግ ስራ ሊጠናከር ይገባል ብለዋል።
የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ የጤና ልማት ዕቅድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዋስሁን እንደገለጽት በመረጃ ጥራትና ፍጥነት ላይ የሚንሰራው ዲጅታላይዜሽን ውጤት እስከሚያመጣ ድረስ ወጥ አቋም በመያዝ እንዳለበት ገልጸዋል።
ከቀበሌ ጀምሮ ያለው የጤና መረጃ ተመሳሳይ እንዲሆን የሚሰራ እና ሌሎች ለስራ እንቅፋት የሆኑን ጉዳዮች በዝርዝር ለይቶ ለውሳኔ የሚያቀርብ ቴክኒካል ወርክንግ ግሩፕ/TWG/ ተቋቁሞ ወደ ስራ የሚገባ መሆኑም ጠቅሰዋል አቶ ዋስሁን።
በጤና ተቋማት ጥራት ያለውን መረጃ የመጠቀም ልምዶች እየተሻሻለ የመጣ ቢሆንም በአንድንድ አከባቢዎች የኢንተርኔት አቅርቦት ማነቆዎች መረጃዎችን በወቅቱ እንዳያደርሱ በማድረጉ ለውሳኔ አሰጣጥ እንቅፋት ቢሆንም የጤና መረጃ ከሰው ህይወት ጋር የተያያዘ በመሆኑ ችግሩ እስከሚቀረፍ ድረስ የጤና ተቋማት የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ለውሳኔ ሰጭ አካላት የማድረስ ግዴታ አለባቸው ብለዋል።
ለውይይቱ መነሻ የሚሆን ሰነድ በአቶ ገበየሁ ደጀኔ እና የክልሉ ጤና ቢሮ የጤና ልማት ዕቅድ ውስጥ የጤና መረጃ ስርዓት ቡድን መሪ የሆኑት በአቶ ምህረቱ በላይ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።
በቀረበው ሰነድ ላይ ተወያዮች አስተያየት የሰጡ ሲሆን በተለይ ወጥ የሆነ መረጃ የመሰነድና አላላክ ስርዓት ላይ አንድ አይነት ግንዛቤ መፈጠር እንደሚገባና ይንን ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።