በጤና ጣቢያዎች የሚሰጡ አገልጎሎቶች ህሰቡን የሚያረካና ከአድሎ የፀዳ መሆን እንዳለበት ተገለጸ።
የጤና ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥን በሚመለከት ክላስተራዊ የህዝብ ኮንፈረንስ በአንገላ ከተማ ተካህዷል።
የመድረኩን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ላቀው መንግስት ህዝብ ጋር ተቀናጅቶ ለመስራት ጤና ተቋማትን ጨምሮ ሌሎች አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ሀላፊነታቸውን በአግባቡጨመወጣት አለባቸው ብለዋል።
አቶ ላቀው ለገሰ ኮንፈረንሱ ውጤታማ እንደሆነ ጠቅሰው ተሳታፊዎችንም በማመስገን ወረዳውን የሚመለከቱ የተነሱ ችግሮችን ለመፍታት ቃል የገቡ ሲሆን ህዝቡ ግን ወቅቱ ሳያልፍ አነስተኛ የማዐጤመ መዋጮ ከፍሎ ተጠቃሚ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።
የወረዳው መንግስት ችግሮችን ለቅመው በመውሰድ ለሚመለከተው አካል ሁሉ የድርሻውን በመስጠት ችግሮችን ለመፍታት ኃላፊነት እኖደሚሰሩ ገልጸዋል።
የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና የጤና ጥ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተመስገን ሰብሮ በጤና ጣቢያዎች የሚሰጠው አገልግሎት ህዝብን የሚያረካና ከአድሎ የፀዳ መሆን እንዳለበት ገልጸዋል።
የአንገላ ጤና ጣቢያና በስሩ የሚገኙ 6 ጤና ኬላዎች እንዲሁም 1 ኮምፕሬሄንሲቭ ሄልዝ ፖስት ተቋማት የ6 ወር ሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።
በዚሁ ሪፖርት እንደተገለጸው ጤና ጣቢያው በ6 ወር 1,414,000 ብር ገቢ መሰብሰቡን የጠቆሙት የአንገላ ጤና ጣቢያ ኃላፊ አቶ አበጀ አታሮ የእቅዱን 200% ማሳካታቸውን ተገልጿል ።
የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች እንደገለጹት ህዝቡን ያስመረሩ በተቋማት ላይ የሚስተዋሉ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን መስተካከል እንዳለባቸው ገልጸዋል።
በተጨማሪም በከንገላ ክላስተር የትራንስፖርት ችግር፣ ለባለሙያዎቹ ዲዩቲና ሰብአዊ ክፍያ በወቅቱ ያለመከፈል፣ የባለሙያ እጥረት እና የስነምግባር ግድፈት፣ የመድኃኒት እጥረትና ሌሎች መስተካከል እንዳለባቸው በውይይቱ ተጠቁሟል።
ኮንፈረንሱ የዛባ ጋዞ ወረዳ አስተባባሪ አካላት፣ የወረዳ አመራሮች፣ የምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች፣ ከ8ቱ ቀበሌያት የመጡ የቀበሌ አመራሮችና የማህበረሰብ ተወካዮች፣ የአንገላ ጤና ጣቢያ ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ዘገባው የዛባ ጋዞ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው