ከ2 ሚሊዮን 534 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ህገ ወጥ መድሀኒት መያዙን የክልሉ ጤና ቢሮ ገለፀ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በካፋ ዞን ከ2ሚሊዮን 534 ሺህ ብር በላይ ግምት ያለው መድኃኒት በቁጥጥር ስር ማዋሉ የክልሉ ጤና ቢሮ ገልጿል።
የክልሉ ጤና ቢሮ እንደ ሀገርና ክልል የበሽታ ጫና የሆነውን የወባ በሽታ ከመከላከሉ እና ከመቆጣጠር ሥራ ጎን ለጎን የመድኃኒት ቁጥጥር ስራዎችን እያካሄደ መሆኑን የክልሉ ጠና ቢሮ ጤናና ጤና ነክ ግብአት ቁጥጥር ባለሥልጣን የምግብና መድሀኒት ቁጥጥር ባለሙያ አቶ ማርቆስ ፎላ ተናግሯል፡፡
የተያዙ መድሃኒቶች በሀገር ውስጥ አገልግሎት እንዲሰጡ ያልተመዘገቡ፣ ፈዋሽነታቸው ያልተረጋገጡ የወባ እና የሌሎች ተላላፊ በሽታዎች መድሀኒቶች መሆናቸውን አቶ ማርቆስ የጠቆሙት፡፡
መድሀኒቶቹ በግል ጤና ተቋማት አገልግሎት እየሰጡ ያሉ በኮንትሮባንድ እና በህገወጥ መድሀኒት ዝውውር የቀረቡ እንዲሁም መረጀ የሌላቸው እና ምንጩ የማይታወቅ ግምታዊ ዋጋ ከ2ሚሊዮን 534 ሺህ 845 ብር የሚያወጣና በካፋ ዞን ባሉት የግል ክሊንኮች በቁጥጥር ተይዘዋል ብለዋል፡፡
መድሀኒቱ ሊያዝ የቻለው ሐምሌ 10 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከዞን ጋር በተደረገው ድንገተኛ የመድኃኒት ቁጥጥር መሆኑን እንደሆነም ነው የክልሉ መድሀኒት ቁጥጥር ባለሙያ አቶ ማርቆስ ፎላ ያብራሩት፡፡
ህብረተሰቡ ፈዋሽነታቸውና ደህንነታቸው ባልተረጋገጠ መድሃኒቶች እየተካመ ላልተፈለገ ውስብስብና ለጤና ችግርና ለሞት እየተደረገ መሆኑን መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ህብረተሰቡ ህክምና በሚደረግበት ወቅት ፈዋሽነታቸውና ደህንናታቸው ባልተረጋገጠ መድሀቶች ከመታካም ጥንቃቄ እንዲያደርግና በህጋዊ መንገድ በተመዘገቡ ተቋማት ህክምና አገልግሎት መግኘት እንደሚገባ አቶ ማርቆስ አሳስበዋል፡፡
በካፋ ዞን ካሉት ከጊምቦ ወረዳ፣ ከጨና ወረዳ፣ ከዋቻ እና ከአውራዳ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ 23 ጤና ተቋማት ከክልሉ ጋር በተደረገው የመድኃኒት ቁጥጥር የተያዙ መድሀኒቶች መሆናቸውን የዞኑ ጤናና ጤና ነክ ግብዓት ቁጥጥር ባለሙያ አቶ አብርሃ ሀይሌ ገልጸዋል።
በእነዚህ መድሀኒቶች ምክንያት ህብረተሰቡ የበለጠ አቅሙን ጨርሶ ደክሞ ወደ ሆስፒታልና ጤና ጣቢያዎች እየመጣ በመሆኑ ለአካል ጉዳታኝነት እና ለከፋ ጤና ችግር እየተገለጠ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
በእንዲህ ተግባር የሚሳተፉ የግል ጤና አገልግሎት መስጫ ተቋማት ህብረተሰቡን የተወሳሰበ የጤና ችግር የሚያስከትለውን ምንጩ ካልታወቀ መድሀኒት አቅርቦት እንዲቆጠቡ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
ዘገባው:- የደ/ምዕራብ ኮሚኒኬሽን ነው