ወባን የማጥፋት ዘመቻ ውጤታማ እንዲሆን ሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በመሙላት ተቀናጅቶና ተናቦ በመስራት እንዳለበት ተገለፀ።
የወባ ወረርሽኝ የመከላከልና የመቆጣጠር ዘመቻ ስራ በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ ሠላም ቀበሌ ተካሂዷል ።
የወባ ትንኝ መራቢያ የሆኑ ቦታዎችን በማፅዳት ውሃ የሚያቁሩ ቦታዎችን በመቆጣጠር በሰው ጤና ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ማስቀረት እንደሚቻል በዘመቻው የተሳተፉ አካላት ተናግረዋል ።
የወባ በሽታን የመከላከል ስራው በሁሉም መዋቅሮች በማካሄድ ለውጥ እንዲመጣ በተገቢው መስራት እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል።
በእለቱም የወባ ትንኝ መራቢያ የሆኑ ቦታዎችን የማፅዳት ስራ ፣ ውሃ የሚያቁሩ ቦታዎችን የማፋሰስና የማዳፈን ጨምሮ ሌሎች ተጨማሪ ስራዎች ተከናውኗል።
የዘመቻ ስራው አንዴ ተጀምሮ የሚቆም ሳይሆን የሁልጊዜ ተግባር መሆን እንደሚገባም በዘመቻው የተሳተፉ አካላት ተናግረዋል።
የመከላከል ዘመቻው በዞኑ በሁሉም አካባቢዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተጠቁሟል ።
ዘገባው የሸካ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።