የህብረተሰቡን ጤና አደጋዎች ቅኝት እና ምላሽ ስራ ክፍል የመረጃ ፍሰት ስርዓት ለማስጠበቅ የከተማ የጤና ዩኒት የውል ስምምነት ከጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ጋር አደረገ።
የውል ስምምነቱ ከምዕራብ ኦሞ ዞን ጤና መምሪያ በተዘጋጀ የህብረተሰቡን ጤና አደጋዎች ቅኝት እና ምላሽ ስራ ክፍል የመረጃ ፍሰት ስርዓት ለማስጠበቅ የተዘጋጀ የውል ስምምነት በመሆኑ የከተማ የጤና ዩኒት ከጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ጋር የውል ስምምነት አደርጓል።
በቦታው የባቹማ ከተማ አስተዳደር ማህበራዊ ክላስተር ሃላፊ አቶ አስማማው አበራ ፣ የከተማው ጤና ዩኒት ሃላፊ አቶ አሸብር አሻግሬ ፣ የባቹማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ደምሴ ሳፒ እንዲሁም በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ አምስት ቀበሌያት ያሉ የጤና ኤክስቴሽን ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
ዘገባው የምዕራብ ኦሞ ዞን መንግስስ ኮሙኒኬሽን ነው።
