የህክምና ላብራቶሪ የምርመራ ውጤት ትክክለኛነትን በማረጋገጥ በጤና ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማሻሻል እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።
ላቦራቶሪ ጥራት አስተዳደር ስርአት (Laboratory Quality Management System) ላይ ከስድስቱም ዞን ለተወጣጡ ላብራቶሪ ባለሙያዎች በክልሉ ጤና ቢሮ ለተከታታይ ቀናት በታርጫ ከተማ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል።
የላብራቶሪ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኡቴ ሬታ እንደገለጹት የላብራቶሪ የምርመራ ውጤት ትክክለኛነትን በማረጋገጥ በጤና ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማሻሻል እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
አቶ ኡቴ አክለው እንደገለጹት በስልጠናው በሁሉም ዞኖች ውስጥ ከሚገኙ ከተመረጡ 24 የጤና ተቋማት የተወጣጡ የላብራቶር ባለሙያዎች ተሳታፊ እንዲሆን ተደርጓል ።
የተመረጡ 24 የህክምና አገልግሎት ሰጭ ጤና ተቋማት ከፍተኛ ተገልጋይ የሚያስተናግዱ እና የስራ ጫና ያለባቸው የጤና ተቋማት ናቸው ብለዋል።
የላብራቶሪ ቁጥጥር ስርአት አስተዳደር ስልጠና መስጠት ያስፈለገበት ዋና ዓላማ ለህብረተሰቡ የተረጋገጠና ታማኝ የህክምና አገልግሎት እንዲሰጥ ለማስቻል እንደሆነም ገልጸዋል አቶ ኡቴ ሬታ።
የቲቢ ላቦራቶሪ ባለሙያና የስልጠና አስተባባሪ አቶ መብራቱ ተፈራ የስልጠና ተሳታፊ የሆኑት የላብራቶሪ ባለሙያዎች ከሚሰጠው ስልጠና ልምድ በመቅሰም የተጣለባቸውን ሙያዊ ሀላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ ያስችላቸዋል ብለዋል።
በተለይ ከምርመራ ውጤት ጋር ተያይዞ በተገልጋዮች ዘንድ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመፍታት እንደሚረዳ አቶ መብራቱ ገልጸዋለ።
አንዳንድ ሰልጣኞች እንደገለጸለት ከስልጠናው የቀሰሙት እውቀት ለቀጣይ ስራ እንደሚያነሳሳቸውና ሀላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ እንደሚያደርጋቸው ተናግረዋል።
በመጨረሻም ለተከታታይ በታርጫ ከተማ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።