የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ጤና ጽህፈት ቤት የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ተግባር አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተካሄደ።

ጽህፈት ቤቱ በ2017 ዓ/ም የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን የተከናወኑ ተግባራትን ሪፖርት ለባለድርሻ አካላት ያቀረበ ሲሆን ተግባሩ ያለበት ደረጃ ተገምግሟል።
በመድረኩ የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሞገስ ሻምበል፣ የከተማ አስተዳደሩ ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ ምርታለም ደሳለኝ፣ የከተማ አስተዳደሩ ጤና ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ወንድሙ አይሳን ጨምሮ ሌሎች የከተማ አስተዳደርና የቀበሌ አመራሮች፣ የዞን ጤና መምሪያ ደጋፊ ባለሙያዎችና የከተማ አስተዳደሩ ጤና ጽህፈት ቤት ማናጅመንት አካላት ተገኝተዋል።
በመድረኩ ሪፖርት ያቀረቡት የከተማ አስተዳደሩ ጤና ጽህፈት ቤት የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አስተባባሪ አቶ ብርሃኑ ሰጉዴ እንደገለጹት በበጀት ዓመቱ የተደረሰበት አጠቃላይ የአባላት ምጣኔ እቅድ 12 ሺህ 162 ሲሆን ክንውን 3 ሺህ 285 ሲሆን የእቅዱ 27 በመቶ ላይ ይገኛል ብለዋል።
ከእቅድ አፈጻጸም አኳያ በቀጣይ ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው እስከ ቀጠና ባለው መዋቅር ወርዶ የተጀመረውን ስራ በማጠናከር ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባ በመድረኩ ተነስቷል።
በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን በከፍተኛ ከተመደቡት 2ሺህ 432 መካከል 190፣ በመካከለኛ 8 ሺህ 27 ታቅዶ 1ሺህ 391 አባላትን ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለ መ
ሆኑ የተገለጸ ሲሆን በዝቅተኛ 1ሺህ 703 ታቅዶ 1ሺህ 703 በማከናወን ገንዘቡን በተናጠል ድጎማ በመንግስት መሸፈን ተችሏል ተብሏል።
በዘርፉ ከተያዘው እቅድ አኳያ የተደረሰበት አፈጻጸም የባለድርሻ አካላትን ቅንጅት የሚጠይቅና በቀጣይ በትኩረት መስራት አስፈላጊ መሆኑም በመድረኩ ተነስቷል።
ዘገባው የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።