የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የ2016 ዓ.ም በጀት አመት አፈጻጽም ሪፖርትና የ2017 ዓ.ም ዕቅድ ግምገማ አካሄደ።

የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዲን አቶ ፀጋዬ አትርሴ እንዳሉት ያለፈው 2016 ዓ.ም በጀት አመት እንደ ኮሌጃችን የተሻለ ዉጤት ያስመዘገብንበት አመት ነው ያሉ ሲሆን ኮሌጁ ካለፈቱት አመታት ጋር ሲነጻጸር በተማሪዎች ዲሲፕሊን፣ በመማር ማስተማሩ ዘርፍ፣ በአስ/ር ዘርፍ፣ በግዢ ስርዓት እንዲሁም በመረጃ አደረጃጀትና አያያዝ ዙሪያ ከፍተኛ እምርታ የታየበት ነው ብለዋል።
አቶ ፀጋዬ አክለዉ እንደገለጹት የዛሪዉን ፕሮግራም ከወትሮው ለየት የሚያደርገው ከዚህ ቀደም ኮሌጁን ሲያገለግሉ የነበሩና በጡረታ የተገለሉ ሰራተኞቻችንን በሰራ ላይ በነበሩበት ወቅት ላበረከቱት አስተዋጾ የምናመሰግንበትና እዉቅና የምንሰጥበት መድረክ መሆኑ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።
በመድረኩ ላይም ከደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት የስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮምሽን ጋር በጋራ በመሆን የስራ ባህልን በሚመለከት አጭር ስልጠና የተሰጠ ሲሆን ከስልጠናው መጠናቀቅ በኋልም የኮሌጁ የ2016 ዓ.ም በጀት አመት አፈጻጽም ሪፖርት እንዲሁም የ2017 ዓ.ም ዕቅድ በኮሌጁ ልማት ዕቅድ ቀርቦ ተገምግሟል።
በግምገማዉ ወቅትም ኮሌጁ ከፍተኛ ዉጤት ያስመዘገበባቸው በርካታ ተግባራት እንዲሁም በቀጣይ መሻሻል በሚገባቸዉ ተግባራት ዙሩያ ከተሳታፊው ለተነሱ በርካታ ጥያቄዎች በየዘርፎቻቸዉ ሰፋ ያለ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።
አቶ ፀጋዬ በማጠቃለያቸዉ እንደገለጹት ባለፈዉ በጀት አመት የኮሌጁ መልሶ ማቋቋሚያ አዋጅ እንዲጸድቅ በትጋት ሲሰራበት የነበረበት ዓመት እንደሆነና ይህም በስኬት የተጥናቀቀ መሆኑን ገልጸዉ አዋጁን ለማጽደቅ ለነበረው ጉልህ ሚና የክልሉን ምክር ቤት አመስግዋል።
የኮሌጁ ቦርድን በተመለከት ቦርድ ለማቋቋም በሂደት ላይ እንዳለም አንስተዋል። በመጨረሻም በበጀት አመቱ የላቀ ዉጤት ላስመዘገቡ የስራ ክፍሎች፣ የትምህርት ክፍሎች እንዲሁም መምህራንን የዕውቅና ሰነ ሥርዓት በማካሄድ ተጠናቋል ሲል የዘገበው የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ነዉ።