የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን (ማዐጤመ) አንዱ ለሌላው በተግባር የምንቆምበት የመደጋገፍ ሥርዓት ነው።

የካፋ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪና የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አጥናፉ ኃይሌ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን የ2017 የበጀት ዓመት የአባላት ምዝገባና እድሳትን አስመልክቶ መግለጫ ስጥተዋል።
ሀላፊው በመግለጫቸው እንደገለፁት የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ፕሮግራም መደጋገፍን መሰረት በማድረግ አስቀድሞ በሚከፈል አነስተኛ መዋጮ ለህክምና ከኪስ የሚወጣውን ያልተጠበቀ የጤና ወጪን በመቀነስ ፍትሃዊ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል እንደሆነ ተናግረዋል።
በመሆኑም የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን (ማዐጤመ) አንዱ ለሌላው በተግባር የምንቆምበት የመደጋገፍ ሥርዓት ነው ብለዋል አቶ አጥናፉ።
ማዐጤመ ህብረተሰቡ የህክምና አገልግሎት በተገቢው እንዲያገኝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክትና ሁሉንም ማህበረሰብ የጤና መድን አባል በማድረግና የጤና አገልግሎት አሰጣጥ በማሻሻል የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባም አመላክተዋል።
በዚህም የመክፈልና የመታከም አቅም የሌላቸውን ወገኖች ህክምና አገልጎሎት እንዲያገኙ የሚያግዝ እንደሆነም ገልጸዋል።
ማዐጤመ በዜጎች ላይ የሚደርሰውን ድንገተኛ የህክምና ወጪ እንዲቀንስ ከማስቻሉም ባለፈ ሁሉም ዜጋ ተገቢውን ህክምና እንዲያገኝ ያግዛል ብለዋል።
በዞን ደረጃ በ2016 ዓ.ም ከ1መቶ 76 ሺህ በላይ የማአጤመ ተጠቃሚዎች የጤና አገልግሎት መጠቀማቸውንም አስታውሰዋል አቶ ጥላሁን።
እንደ ዞን በፕሮግራሙ የተገኙ ውጤቶችን ለማስቀጠል የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን የአባላት ምዝገባና እድሳት ንቅናቄ መጀመሩን ያስታወቁት ሀላፊው ባለፉት ዓመታት በማዐጤመ አፈጻጸም የተገኙ መልካም ውጤቶችን በማስቀጠልና ጉድሌቶችን በማረም በ2017 በጀት ዓመት የበለጠ ለማሳካት ጠንክረን መሥራት ይኖርብናል ብለዋል።
በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደ ዞን የተጀመረውን ንቅናቄ በመጠቀም አቅም የሌላቸውን ወገኖች ለመርዳት የተረባረቡትን አካላት አመስግነው ሌሎችም በዚሁ ተግባር ላይ እንድሳተፉ ጠይቀዋል።
”የጤና መድህን አባልነት ለጋራ ብልፅግና“ በሚል መሪ ቃል ለአጭር ጊዜ በሚቆየው የአባላት ምዝገባና እድሳት ንቅናቄ እስካሁን በተለያዩ ምክንያቶች የአባልነት እድሳትና ምዝገባ ያላደረጉ ዜጎችም በቀሪ ጥቅት ቀናቶች ውስጥ የ2017 የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አባል በመሆን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
መግለጫ የካፋ ዞን ብልጽግና ፖርት ቅ/ጽ/ቤት ነው