የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አባል በመሆናችን የሚገጥመንን የጤና እክል በወቅቱ ለመታከም አስችሎናል ሲሉ ተሳታፊዎች ተናገሩ::
በቶጫ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ እየተካሄደ ባለው በህዝብ አስተያየት መድረክ ላይ የተሳተፉ የወረዳው ነዋሪዎች፤ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አባል በመሆናችን የሚገጥመንን የጤና እክል በወቅቱ ለመታከም አስችሎናል ሲሉ ተናግረዋል።
አገልግሎት ካገኙ የጤና መድህን አባላት መካከል አስተያየታቸውን የሰጡን አቶ ለማ መንገሻ ፣ አቶ አስረስ አሻግር እና ወ/ሮ ቀለሟ አመለ እንደተናገሩት የጤና መድህን አባል በመሆናችን በከፍተኛ የጤና ተቋም በመሄድ ጤንነታችንን ከማግኘት ባለፈ የህክምና ወጫችንን ጤና መድህኑ ሸፍኖልናል በዚህም ደስተኛ ነን ብለዋል፡፡
ጤና መድህን አባል ከሆኑ ጀምሮ ማንኛውንም የጤና አገልግሎት በሆስፒታሉ በነፃ ማግኘት በመቻላቸው የነሱንና የቤተሰባቸውን ጤና እንዲጠበቅ አድርጎናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የህመም ስሜት ሲሰማቸውም በገንዘብ እጥረት ምክንያት ከጤና ተቋማት እንዳይርቁ እንዳስቻላቸውም ገልፀዋል፡፡
አቶ እሸቱ ክዳኔና ወ/ሮ ብርቅነሽ ደድሶ በሰጡት አስተያየት ባለፉት አመታት የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አባል በመሆናችን እጃችን ላይ ገንዘብ ባይኖርም በቤተሰቦቻችን ላይ የሚደርሰውን የጤና እክል በወቅቱ በመታከም ሊደርስ የሚችለውን የማህበራዊና የኢኮኖሚያዊ ችግር ማስወገድ ከመቻሉም በላይ የቤተሰቦቻችን ጤና ማስጠበቅ በመቻላችን ተጠቃሚ ሆነናል ነው ያሉት።
አስተያየት ሰጭዎቹ አክለውም የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አባል ያልሆኑ ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎችም አባል በመሆን ተጠቃሚ ሊሆኑ እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ዘገባው ፦ የቶጫ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።