የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ውጤታማነት የባለድርሻ አካላት ሚና ወሰኝ እንደሆነ ተገለጸ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ዳውሮ ዞን ማሪ ማንሳ ወረዳ የ2017 በጀት ዓመት የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን የአባልነት ምዝገባ እስካሁን ያለበት ደረጃ ተገመገመ።
በየደረጃው ያለውን የአፈጻጸም ክፍተት በማረም ህብረተሰቡን የማህበረሰብ ዐቀፍ ጤና መድህን አባል በማድረግ በኩል ትኩረት ተሰጥቶት መሠራት እንዳለበት እና የህብረተሰቡን የአመለካከት ክፍተት ለመሙላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በትኩረት እንዲሰራበትም የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተካልኝ በቀለ ተናግረዋል።
ማህበረሰቡ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ እድሳቱን እና አባልነቱን በማከናወን ከድንገተኛ ህክምና ወጪ መዳን እንደሚገባው በማኅበረሰቡ ግንዛቤ መፍጠር ላይ መሰራት እንዳለበት አስተዳዳሪው ገልጿል።
የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድን አገልግሎት ተግባራዊ በማድረግ ፍትሐዊና ጥራቱን የጠበቀ የጤና አገልግሎት ለሁሉም ነዋሪዎች ማድረስና ሁሉ አቀፍ የጤና ሽፋን እዉን ለማድረግ ጠንክረን መስራት አለብን ያሉ የመንግስት ዋና ተጠሪና የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አወቀ አይሳ ናቸው።
ለዚሁ ዓላማ መሳካትና ለተግባራዊነቱ የባለድርሻ አካላት ተገቢ ሃለፊነታቸዉን እንዲወጡም አሳስበዋል አቶ አወቀ፡
ነዋሪዎች የጤና መድህን አገልግሎት አባልነት ምዝገባን በቀሩት ቀናት እንዲያከናውኑና ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት ማህበረሰቡ የጤና መድህን አባል በመሆን ራሱንና ቤተሰቡን ካልታሰበ ድንገተኛ ወጪ በመጠበቅ ለጤናው ዋስትና መያዝ ይገባዋል ሲሉ የጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በረከት ባቡሎ አስገንዝበዋል፡፡
ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተነሣሽነትና በቁርጠኝነት ፈጥኖ ወደ ተግባር በመግባት ህብረተሰቡን የጤና ተጠቃሚ የሚያደርግ ሥራ መሥራት እንደሚገባ መልዕክት ተላልፏል።
የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን የነባር አባላት እድሳት እና የአዲስ አባላት ምዝገባ ያለበት ደረጃ የወረዳው አመራር አካላት ፣ የጤና ጣቢያ ኃላፊዎች እና የጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ማናጅመንት በተገኙበት ተገምግሟል።
ዘገባው :-የወረዳው መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ነው።