የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት የህ/ሰቡን ጤንነት ለማስጠበቅ የሚያስችል በመሆኑን ግንዛቤ በመፍጠር ተግባሩን ማስፋት ይገባል ተባለ።

የ2017 በጀት ዓመት ማአጤመ ገቢ አፈጻጸም ላይ ያለውን እንቅስቃሴ በተመለከተ በወረዳው ማዕከል ግምገማ እየተካሄደ ነው።
የሰሜን ቤንች ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ስንታየሁ በፍቃዱ እንደገለፁት ባለድርሻ አካላት የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ላይ ያለውን አመለካከት በማጥራት አፈጻጸሙ ሊስተካከል ይገባል ሲሉ ተናግረው የድሀ ድሀ አካላትን ለመደገፍና የማአጤመ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ ሌሎችን በማስተባበር ገንዘቡን ቶሎ ገቢ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
ዋና አስተዳዳሪው አያይዘውም የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት የህ/ሰቡን ጤንነት ለማስጠበቅ የሚያስችል በመሆኑን ግንዛቤ በመፍጠር ተግባሩን ማስፋት ይገባል ብለዋል።
የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን የህዝቡን ጤናንት ለማስጠበቅ የሚችል መሆኑን ግንዛቤ በመፍጠር ሊሰራ ይገባል በማለት ተናግረዋል።
የሰሜን ቤንች ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ኢንጂነር ጌራ ባርናባስ በግምገማው መደረክ እንዳሉት ጤናማ የሆነ ትዉልድ ለመፍጠር እና ሃገራችን የጀመረችዉን የብልጽግና ጉዞ እዉን ለማድረግ ማህበረስቡን የጤና መድህን ተጠቃሚ ማድረግ ይጠበቅብናል ሲሉ ሀሳባቸውን ገልጸዋል።
የአፈጻጸም ግምገማ የቀበሌው ሥራ አስክያጅ አፈፃፀም ሪፖርት እየቀረቡ ሲሆን ህ/ሰቡ የጤና መድህን ተጠቃሚ ለማድረግ የሁሉንም ሰዉ እርብርብ የሚጠይቅ ነዉ ብለዋል።
የጤና መድህን በተቀመጠለት አሰራር መሰረት ማህበረሰቡን በሃብቱ መጠን ለይቶ ከማስከፈል አኳያ እና የተሰበሰበው መዋጮ ብር ከማስገባት አኳያ ያሉ ክፍተቶች መስተካከል እንዳላባቸው በግምገማው ተገልጿል።
የ2017 በጀት ዓመት የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት በወረዳው ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የሰሜን ቤንች ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኮማንደፖት አቶ ባስልኤል ተሰማ በዝርዝር ያቀረበ ሲሆን ተግባሩን ለማሳደግ በጥንካሬና በድክመት ቀርቧል።
በማአጤመ ገቢ አሰባሰብ እንቅስቃሴ ላይ በጥሩ አፈጻጸም የተመዘገቡ እንዳሉ ሁሉ ዝቅተኛ አፈጻጸምና የተሰበሰበውን ገንዘብ በአግባቡ ያላስገቡ እንዳሉም ማወቅ እንደተቻለ በግምገማ ወቅት ታውቋል።
ማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ያለው ጠቀሜታ በቃል የሚነገር እንዳልሆነ በግምገማው ተገልጾ እያንዳንዱ ባለድርሻ አካላት ተግባሩ ላይ በትኩረት በመስራት የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል።
ተሳታፊዎችም የቀረበው የግምገማ ግብረ መልስ የወረዳው ነባራዊ ሁኔታ የሚገለጽ ስለሆነ ወስደን በቀጣይ ባለን አጭር ጊዜ ውስጥ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በትኩረት እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል።
በመድረኩ ማጠቃለያ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ስንታየሁ በፍቃዱ ፣የሰሜን ቤንች ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ኢንጂነር ጌራ ባርናባስ ፣የወረዳው ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ ፈጠነ ባይከዳ ጨምሮ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተነሱት ሀሳብና በቀረበው ሪፖርት ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የ2017ዓ/ም የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አፈጻጸም ግምገማ የወረዳዉ ጠቅላላ አመራር፣የዞን ደጋፊ ባለሙያዎች ፣የጤና ጽ/ቤት ማኔጀመንት ፣የማዐጤመ ኤጀንሲ ተቋም ባለሙያ፣የጤና ጣቢያ ኃላፊዋች፣የጤና ሰፑርባይዘሮች፣የቀበሌ አመራሮች፣አጠቃላይ ጤና ኤክሰቴንሽን ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል።
ዘገባው ሰሜን ቤንች ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ነዉ።