“የምትተክል ሃገር የሚያፀና ትውልድ” በሚል መርህ ቃል በተከናወነው የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ጎን ለጎን በዳውሮ ዞን የተርጫ ደም ባንክ አገልግሎት አማካይነት ከበጎ ፍቃደኞች የደም ልገሳ መርሃ ግብር ተከናውኗል።

በደ/ም/ኢ/ት/ህ/ክ/መንግስት በአንድ ጀምበር 18.9 ሚሊዮን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ላይ የክልሉ ጤና ቢሮ ከፍተኛ አመራሮች እና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።
የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም አሻራቸውን ሲያስቀምጡ ባስተላለፉት መልዕክት በአገራችንና በአለም ላይ የአየር ንብረት መዛባትን ተከትሎ ሙቀት እየጨመረ ፣ጎርፍ እና የመሬት ናዳ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣቱ ምክንያት በቂ ዛፍ ያለመትከላችን እንደሆነ ገልጸዋል።
በመሆኑም የከተፈጥሮ የአየር ሚዛን መዛባት ተከትሎ በሰው፣ በእንስሳትና በእጸዋት ላይ አየደረሰ ያለውን አደጋ ለማስቀረት ሁሉም ሰው በያለበት ችግኝ መትከልና ተከታትሎ ማሳደግ አለበት ብለዋል።
ችግኝ መትከል ለክልላችን ትልቅ ትርጉም አለው ያሉት ሀላፊው አገራችን የአለማቀፍ አሬንጓዴ እንሽየትቪ መርሀ- ግብር ተግባራዊ በማድረግ በአለም አቀፍ ደረጃ የሚትታወቅ በመሆኑ አሁን መትከል ብቻ ሳይሆን የተተከለውን በአግባቡ በመንከባከብ ብልጽግናችን እናረጋግጣለን ብለዋል።
ችግኝ መትከል የአየር ንብረት ለውጥን ከማሻሻል ባሻገር ለሰው ልጆች ከፍተኛ የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ የሚያስችል ተግባር ነው ያሉት አቶ ኢብራሂም ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን ችግኞችን የመትከል ልምዳችን ማዳበር አለብን ብለዋል።
ክልላችን በአገራችን ብሎም በአለም አቀፍ ደረጃ በደን ሽፋን የምትታወቅና የቡና መገኛ በመሆኗ ቀደምት አባቶች ጠብቆ ያቆዩ ደኖችን እኛም ተክለንና ጠብቀን ለትውልድ ማስረከብ ይገባናል ብለዋል።
የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ በዚሁ የተከላ መርሃ ግብር የተያዘውን የችግኝ ተከላ ዕቅድ ከማሳካት በተጨማሪ ከዚህ ቀደም የተተከለውን ችግኞች ከሰውና ከእንስሳት ንኪኪ ለመጠበቅ ከህብረተሰቡ ጋር አብረን እንሰራለን ብለዋል።
የህንን የችግኝ ተከላ ኘሯግራም ከሌላ ጊዜ ለየት የሚያረደርገው የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ የሚያስችሉ የተለያዩ የፍራፍሬ ዛፎች ላይ ትኩረት ተደርጓ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል።
“የምትተክል ሀገር የሚያጸና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት በአንድ ጀምበር 18.9 ሚሊዮን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል አቶ ዳዊት።
በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የዳውሮ ዞን ማራቃ ወረዳ ምርጫ ክልል ተወካይ እና በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት እንዱስትሪና ማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሆኑት ዶ/ር አማረች በካሎ ባስተላለፉት መልዕክት የአረንጓዴ አሻራ የማስቀመጥ ልማዳችንን ጠብቀን የተተከሉ ቾግኞችኖ ተንከባክበን አለማችንን በሙቀት ከሚመጣው ጥፋት መታደግ አለብን ብለዋል።
በመርሀ_ ግብሩ አገራዊ እና ክልላዊ ጥሪ ተግባራዊ በማድረግ በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት ብዝሀ ከተሞች ውስጥ አንዷ በሆነችው ታርጫ ከተማ የማገኙ የክልል ቢሮዎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ሠራተኞች፣ የዳውሮ ዞን ወክለው በፖርላማ የማገኙ ምክር ቤት አባላት ፣የክልሉ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ ፣ የዳውሮ ዞን አስተዳዳር፣ የዳውሮ ዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የማረቃ ወረዳ አስተዳዳሪ፣ የስራ ኃላፊዎች ፣ መዳ ኩይሊ ቀበሌ ነዋሪዎችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተው አረጓዴ አሻራቸውን በማረቃ ወረዳ በማዳ ኩይል ቀበሌ አኑረዋል።