የሳይለም ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት በ2016 በጀት ዓመት በአጠቃላይ ጤና አገልግሎት ባስመዘገበው ዉጤት ከኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር የዕውቅና እና የምስጋና ሽልማት ማግኘቱ ተገለጸ::
ካፋ ቴሌቪዥን) የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ከማል ጠይብ ከጣቢያችን ጋር በስልክ ባደረጉት ቆይታ ወረዳዉ በአጠቃላይ የጤና አገልግሎት ዘርፎች በክልሉ ከፍተኛ ዉጤት በማስመዝገብ ከኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር የዕውቅና እና የምስጋና ሽልማት አግኝቷል ብለዋል።
የእናቶችን ሞት መቀነስ፣ እናቶች በጤና ተቋም እንዲወልዱ ማድረግ፣ የአካባቢ ጤና መጠበቅ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ ሽንት ቤቶችን በአካባቢው መገንባት፣ በበሽታ መከላከል፣ አክሞ ማዳንና ሌሎች የለዉጥ ስራዎች ተቋሙ ስኬት ያስመዘገበባቸዉ ዘርፎች መሆናቸውን ተናግረዋል።
በዚህም ወረዳው የጤና ሚኒስቴር ባዘጋጀው የ2016 ዓ/ም አጠቃላይ አፈጻጻም ግምገማ የላቀ ዉጤት በማስመዝገቡ ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የ6 ኮምፒውተሮች ሽልማትና የምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል ብለዋል።
ወረዳው ይህንን ዕዉቅና እንዲያገኝ ሙሉ አቅማቸውንና ጊዜያቸዉን በመስጠት ዉጤታማ ተግባራትን ላከናወኑ በየደረጃው ለሚገኙ አካላት አቶ ከማል ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ዘገባው የወረዳው መ/ኮ/ጽ/ቤት ነው::