-የአለም ጤና ድርጅት በሚዛን አማን ከተማ ጤና ጽህፈት ቤት ስር ለሚገኙ ሁለቱ ጤና ጣቢያዎች የወባ ህክምና መድሃኒቶችንና ለምርምራ የሚሆኑ ግብአቶችን ድጋፍ ማድረጉ ተገለጸ።
ግምታዊ ዋጋው ከ448 ሺህ 740 ብር በላይ ሲሆን ግብአቱ የተደረገላቸው ለሚዛንና ጋቸብ ጤና ጣቢያዎች እንደሆነ ተገልጿል።
የህክምና ግብአቶቹ ፍትሃዊ ሆነው ለሁለቱ ጤና ጣቢያዎችና ጤና ኬላዎች መከፋፈል እንዳለባቸው የሚዛን አማን ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ሞገስ ሻምበል ገልጸዋል።
የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሞገስ ሻንበል፣ የጤና ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ወንድሙ አይሳን ጨምሮ የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች፣ በዞን ጤና መምሪያ የሚዛን አማን ከተማን የሚደግፉ ባለሙያዎች በሚዛን ጤና ጣቢያ የየፋርማሲና የምግብ እጥረት ያለባቸውን ህጻናት ህክምና ክፍሎች ጎብኝተዋል።
ጉብኝቱን አስመልክቶ ገለጻ ያደረጉት የከተማ አስተዳደሩ ጤና ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ወንድሙ አይሳ የወባ ወረርሽኝን ለመከላከል የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ የአለም ጤና ድርጅት ድጋፍ በማድረግ የጀመረውን የመድሃኒትና የላብራቶሪ ምርመራ ግብአት አጠናክሮ እንሚቀጥል ገልጾልናል ብለዋል።
የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ለጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች በወባ ምርመራና ህክምና ዙሪያ ለጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ስልጠና በመስጠት በዘርፉ ይታይ የነበረውን የክህሎት ክፍተት መሙላት አስችሏል ብለዋል ሃላፊው አክለው።
በሚዛን ጤና ጣቢያ ከፍተኛ የምግብ እጥረት ያለባቸው ህጻናት ተለይተው የህክምናና የምግብ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን የሚዛን ጤና ጣቢያ ሃላፊ ወ/ሮ እርጎዬ ገብሬ ገልጸዋል።
በፈየአለም ጤና ድርጅት ያደረገው ድጋፍ ለጤና ጣቢያዎችም ሆነ ለጤና ኬላዎች በወባ ምርመራና ህክምና አልፎ አልፎ የሚከሰተውን የግብአት አቅርቦት ችግር የሚቀርፍ መሆኑም ተገልጿል።
ዘገባው የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።