የኢት/ያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የስራ አመራር ቦርድ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያየ::

በገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሺዴ ሰብሳቢነት የሚመራዉ የአገልግሎቱ የስራ አመራር ቦርድ መደበኛ ስብሰባዉን የአገልግሎቱ ከፍተኛ አመራሮች እና የማኔጅመንት አባላት በተገኙበት በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ዉይይት አካሂዷል፡፡
በዉይይቱ በንዑስ ኮሚቴ የታዩ የክምችት እና የስርጭት እንዲሁም ጥቅም ላይ የማይዉሉ ግብአቶች ማቀጠያ መመሪያዎችን ቦርዱ ያፀደቀ ሲሆን ፤ አሁን ላይ የዉጭ ምንዛሬ በመጨመሩ ለግዥ ስርአቱ ጫና እንዳይፈጥር ተጨማሪ በጀት ቀርቦ ቦርዱ አፅድቋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የ2016 ዓ.ም በዉስጥ የተሰራ የኦዲት ሪፖርት እና በፌደራል ዋና ኦዲተር የተሰራ የኦዲት ግኝት በዝርዝር ቀርቦ የተገመገመ ሲሆን ፤ ያለውን በቀጣይም በኦዲት ግኝቶች ላይ Action plan ቀርቦ የሚመለከታችው የሰራ ክፍሎች ማሻሻል ያለባችውን በዝርዝር እንድቅርብ አቅጣጫ ስተዋል።
መንግስት የኢኮኖሚ ለዉጥ(Reform) እያደረገ በመሆኑ ምንም አይነት የመድኃኒት አቅርቦት መቆራረጥ እንዳይከሰት ቅድመ ግዥ ማከናወን እንደሚገባ እና በዛዉ ልክ የቁጥጥር ስራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል ሊሰራ ይገባል ሲሉ አቶ አህመድ ሺዴ ተናግረዋል፡፡
በዉይይቱ ማጠቃለያ የ2016 ዓ.ም በጀት አመት የክምችት መዝጊያና የ2017 ዓ.ም በጀት አመት መክፈቻ ሪፖረት ላይ አቅጣጫ በመስጠት ፤ የግዥ ስርአት ረቂቅ መመሪያ በንዑስ ኮሚቴዉ እንዲታይ አቅጣጫ በመስጠት ዉይይቱ የተቋጨ ሲሆን ፤ በመጨረሻ የስራ አመራር ቦርዱ መጋዘኖችን እና የካሜራ መቆጣጠሪያ ክሎችን ጉብኝት አድርገዋል፡፡
#ማገልገል ክብር ነዉ
ምንጭ EPSS FB