የኦዳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የ2016 ዓም የአጠቃላይ ሰራተኞች ፎረም አካሄደ።

በጠሎ ወረዳ ኦዳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የአጠቃላይ ሰራተኞች ፎረም አካህዷል።
የሆስፒታሉ ስራአስኪያጅ አቶ ሰላሙ ገዳዎ በመክፈቻ ንግግራቸዉ እንደገለፁት የፎረሙ ዋና ዓላማ ከሰራተኞች ጋር በመወያዬት ተግባር ላይ የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት የጋራ መፍትሄ በማበጀት የአገልግሎት ጥራትን ማሻሻል እንደሆነ አብራርተዋል።
አቶ ሰላሙ ገዳዎ ዉይይቱ በዝርዝር የ2016 በጀት ዓመት የታዩ ጠንካራ አፈጻጸም በመለየት ኋላ የቀሩ ተግባራት ለይተው ለቀጣይ ማሻሻያ የሚያስችል ዕቅድ በማቀድ ይገባል ብለዋል።
የጤና ሥርዓት ማነቆ የሆኑ አሰራሮችን ለመፍታት የተዘረጋው ሪፎርም/SBFR/ ማስጀመሪያ ሰነድ ላይ ግልፀኝነት መፍጠር ስለማገባ በሚቀርበው ሰነድ በጥልቀት በመወያየት ወደተግባር መገባት አለበት ብለዋል።
አድሱ የጤና ሥርዓት ማነቆ ተኮር ሪፎርም/SBFR/ በሆስፒታሉ በይፋ ስራ እንድጀምር የተዘጋጀ ሰነድ በሆስፒታሉ ሜድካል ዳይረክተር ዶ/ር ሞኤቦን ጨመዳ የቀረበ ሲሆን የዚህ እንሸቲቭ አአካል የሆነው የባለሙያ አለባበስ መለያ(Dressing code) መሰረት ሆስፒታሉ ያዘጋጀዉ የደንብ ልብስ በይፋ ለብሰው አገልግሎት መስጠት እንዲጀምሩ ተደርጓል ።
በሆስፒታሉ ወደ ትግበራ የተገባዉ የጤና ሥርዓት ማነቆ ተኮር ሪፎርም/SBFR/ መመሪያ ገዥና ጠቃሚ እንደሆነ የተነሳ ሲሆን ከእንሼቲቭ ጋር ተያይዞ ከተቋሙ የሚያስፈልጋቸዉን የድጋፍ ነጥቦችን ባለሙያዎች በአስተያየታቸው አንስቷል።
በቀረበው ሰነድ መሠረት የክትባት አገልግሎት አፈጻጸም፣ የወሊድ አገልግሎት ፣ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት፣ የሳምባ በሽታ ምርመራና ህክምና አገልግሎት ላይ የተሻለ አፈጻጸም መመዝገቡ ተመላክቷል።
የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ምርመራ፣ የረጅም ጊዜ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት፣ እናቶች እንደወለዱ ከ24-48 ሰዓት ድረስ የሚሰጠው የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ቀጣይ መሻሻል እንዳለበት በዉይይቱ ተነስቷል።
በመድረኩ የተለያዩ ዉሳኔዎች የተላለፉ ሲሆን ከነኝህም በዋናነት ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ፅኑ ህሙማን፣ ለህክምና አገልግሎት አቅም ለሌላቸውና ለሌሎች ድጋፍ ለሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች የሆስፒታሉ ሰራተኞች ወርሃዊ መዋጮ በማዋጣት ያልተቋረጠ በጎ አድራጎት ሥራ እንደሚሰራ ተገልጿል።
በስተመጨረሻም የሆስፒታሉ ስራአስኪያጅ በ2016 በጀት ዓመት የተሻለ አፈጻጸም እና ርህራሄ የተሟላ አገልግሎት የሰጡ ሰራተኞችን ከየስራ ክፍል በመለየት ዕዉቅና የሰጡ ሲሆን በቀጣይ ሁሉም ሰራተኛ በየስራ ክፍሉ ለማህበረሰቡ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ተግቶ መስራት እንዳለበት አሳስቧል።
ዘገባው የጸሎ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።