የወባን ስርጭት ለመከላከል ከወትሮ በተለየ መስራት እንደሚገባ የማጂ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት አስታወቀ።
ጽ/ቤቱ በዛሬው ዕለት ከጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ጋር ባካሄደው ውይይት መድረክ ላይ የኩብት፣ የቀይኮከብ፣ የኦር፣ የሻልት እና የገልከም ቀበሌዎች አፈፃፀም የቀረበ ሲሆን በጥንካሬ የተለዩ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እንዲሁም በጉድለት የታዩ ትኩረት ተደርጎባቸው ሊፈፀሙ እንደሚገባ ተገልጿል።
የማጂ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ አምሳል ወ/ገብርዔል እንደገለፁት የጤና መረጃ አያያዝና አላላክ ሥርዓታችንን በማሻሻል የመረጃ መፋለስን ለማስቀረት በትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።
በቀጣይ የወባ ስርጭትን ለመከላከል ያቆሩ ውሃዎችን የማፋሰስ፣ የማዳፈን እና አጓበር የማሰራጨት ተግባር ሲከናወኑ መቆየታቸውን ጠቅሰው ነገር ግን የአጎበር አጠቃቀም ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ማረም እንደሚገባ ገልፀዋል።
ክትባት ላልወሰዱ ህፃናት የማካካሻ ክትባት ለመስጠት እንዲያስችል በየቀበሌው የማጥራትና የማረጋገጥ ስራ መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል ሀላፊዋ።
በየቀበሌው የተሰራጨና አገልግሎት ላይ የዋለ አጎበር መረጃ መለየት እንደሚገባ የጠቀሱት ወ/ሮ አምሳል በቀጣይ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጀምሮ ሥራን መሠረት ያደረገና ተጠያቂነት የሰፈነበት የአሰራር ሥርዓት እንደሚዘረጋ ገልፀዋል።
በመድረኩ ማጠቃለያም የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ የመረጃ ፍሰት ሥርዓትን ለማስጠበቅ የወረዳው ጤና ጽ/ቤት ከቀበሌ ጤና እክስቴንሽን ሠራተኞች ጋር የውል ስምምነት ተፈራርመዋል።