የወባ በሽታ ወረርሽኝ ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በካፋ ዞን እየተሰራ ያለው ስራ አበረታች መሆኑ ተገለጸ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ከጤና ቢሮ ጋር በመቀናጀት በካፋ ዞን ወቅታዊ የወባ ወረርሽኝ ቁጥጥር ላይ የተደረገ የመስክ ምልከታ ግብረ-መልስ ለዞኑ አቅርቧል ።
የመስክ ምልከታ ግብረ-መልስ ሪፖርት በክልሉ ጤና ቢሮ የኤች አይ ቪ አድስ መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶረት ዳይሬክተር አቶ መንግስቱ ከሰሪ አቅርበው ውይይት ተደርጓል።
ከቦንጋ ከተማ አስተዳደር ቦንጋ ጤና ጣቢያና ካያ ኬላ ጤና ኬላ፣ ከጊምቦ ወረዳ ዲሪ ጤና ጣቢያና ቤየሞ ጤና ኬላ እና ጨና ወረዳ ኮዳ ጤና ጣቢያና ኮዳ ጤና ኬላ የመስክ መልከታ አካል መሆናቸው ተገልጸዋል።
በዞኑ አሁናዊ የወባ ወረርሽኝ መከላከልና መቆጣጠር ያለበትን ደረጃ ምልከታ በማድረግ ባለድርሻ አካላት አትኩሮት እንዲሰጡት ለማስቻል እንደሆነ በሪፖርቱ አመላክቷል።
የወባ ወረርሽኝ የዕለት ተዕለት የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ በከተማና በገጠር ከፍተኛ ተፅዕኖ እየፈጠረ ያለው በሽታ መሆኑን የካፋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ደመላሽ ንጉሴ ተናግረዋል።
የበሽታ አስከፊነቱን በመረዳት በዞን ደረጃ የወባ ወረርሽኝ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራን በተመለከተ በርካታ የዘመቻና ንቅናቄ ስራዎች ልዩ ትኩረት ተሰጥተው በየደረጃ ያሉ መዋቅሮች ላይ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የተሰጠውን ግብረ መልስ ላይ በጥንካሬ የተገለጹት በማጠናከር እና በጉለት የተስተዋሉ ችግሮችን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ወረርሽኙን ከዞናችን ማጥፋት አለብን ብለዋል።
የመንግስት ተቋማት፣መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የትምህርት ቤቶች፣ የሃይማኖት ተቋማት እና ሌሎችም የወባ በሽታን በዘላቂነት ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተጀመረውን ስራ ተጠናክረው መቀጠል እንደምገባ ምክትል አስተዳዳሪው አሳስቧል።
የወባ በሽታ ወረርሽኝ ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በካፋ ዞን እስከ ታቸኛው መዋቅሮች ድረስ እየተሰራ ያለው ስራ አበረታች መሆኑን የክልሉ ምክር ቤት በጀትና ፋይንናስ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ የኋላሸት በላይነህ ተናግረዋል።
የወባ ወረርኝ ጫና ያለባቸውን ወረዳዎች በመለየት የንቅናቄ መድረኮች እንዲፈጠር ማድረግ፣የአካባቢ ቁጥጥር ስራዎችና ሌሎች የመከላከል ተግባራት እንዲጠናከሩ ማስቻልና የማህበረሰብ ተሳትፎ ለማሳደግ አላማ ያደረገ መስክ ምልከታ እንደሆነም ገልጸዋል።
በዞኑ የወባ በሽታን ለመግታት በሚደረገው ሁለንተናዊ ጥረት በክልሉ ሌሎች አከባቢዎች ተሞክሮ የሚሆን ስራ መሆኑን የተናገሩት ወ/ሮ የኋላሸት የክልሉ ድጋፍና ክትትል ተጠናክረው እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
መድረኩ ላይ የካፋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ደመላሽ ንጉሴ፣የክልሉ ምክር ቤት በጀትና ፋይንናስ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ የኋላሸት በላይነህ፣የዞኑ የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ታከለ ታምሩ እና ወ/ሮ ፅዮን ታዬን ጨምሮ የክልል ፣የዞንና የቦንጋ ከተማ ጤና ባለሙያዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝቷል።
የካፋ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው ።