የወባ ወረርሽኝን በዘላቂነት ለመግታት ከማህበረሰቡ ጋር ተቀናጅቶ መስራት እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ክልል ምክር ቤት ምክትል አፌ-ጉባኤ ወ/ሮ ፀሀይ ዳርጫ አስታወቁ።
የክልሉ ጤና ቢሮ በዳውሮ ዞን ከዞንና የወረዳ መዋቅር የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር የጋራ ምክክር አካሂዷል።
በምክክር መድረኩ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ክልል ምክር ቤት ምክትል አፌ-ጉባኤ ወ/ሮ ፀሀይ ዳርጫ የወባ ወረርሽኝ እያስከተለ ያለውን ጫና በዘላቂነት ለመግታት ሁሉም የባድርሻ አካላት ርብርባቸውን አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል።
የባለድርሻ አካላት መናበብና ቅንጅታዊ አሰራራቸውን ይበልጥ ማዳበር ወረርሽኙን ለመግት ያለው ሚና ከፍተኛ ስለሆነ በየደረጃው የሚገኙ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ህዝባዊና መንግስታዊ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባም አሳስበዋል ።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ የበሽታ መከላከል ዳይሮክቴሬት ዳይሬክተር ዶክተር እንዳለ ሳህሌ በበኩላቸው ወረርሸኙን ለመግታት ቢሮው ህብረተሰቡን በማቀናጀት የመከላከልና የህክምና ሥራዎችን በተጠናከረ ሁኔታ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
ይህንኑን ተግባር ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ የጤና ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጣቸውን ሊያቀላጥፉና ተደራሽነታቸውንም ማሳደግ በሚያስችሉ አግባቦች ላይ እየተሰራ እንደሚገኝም አብራርተዋል።
ወረርሽኙን ለመግታት እየተደረገ ያለው ሁሉን አቀፍ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ያብራሩት ዶክተር እንዳለ ከጤና ኬላ አንስቶ ያሉ ተቋማት ርብርባቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።
የዳውሮ ዞን መንግስት ዋና ተጠሪና የብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታሪኩ አካሉ በበኩላቸው ከአገልግሎት አኳያ በጤና ተቋማት የሚስተዋሉ ውስንነቶችን ለመቅረፍ በትጋት ሊሰራ ይገባል።
ወረርሽኙን በዘላቂነት ለመግታት የሚደረገው ርብርብ የዜጎችን ደህንነት እና ጤንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ከማስጠበቅ ጋር በማዛመድ ሊሰራ ይገባልም ብለዋል።
ስለሆነም በየደረጃው ያሉ የጤና አመራሮች እና የባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን በመከፋፈል በባለቤትነትና በቁርጠኝነት መሰራት እንደምገባቸውም አቶ ታሪኩ ጠቁመዋል።
ወረርሽኙን ለመከላከል የአልጋ አጎበር መጠቀም ሁኔኛ መፍትሔ መሆኑን የገለጹት በዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ የድንገተኛ በሽታዎች ቅኝት ምላሽ አሰተባባሪና አቶ ወልደ በካሎ የማህበረሰቡ ንቃተ ሂሊና ያለመጎልበት ከውስንነቶቹ የሚጠቀስ ነው ብለዋል።
ወረርሽኙን ለመግታት እና ለመቆጣጠር በህብረተሰብ ተሳትፎ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን አጠናክሮ ለማስቀጠል የተቀናጀ ጥረት እንደሚደረግ የምክክሩ ተሳታፊዎች አስረድተዋል።
ከአጎበር አያያዝና አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ ሰፋፊ የግንዛቤ እጥረቶችን ለመፍታት የሚመለከታቸው ሁሉ የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ በምክክሩ ተመልክቷል።
በአንዳንድ መዋቅሮች የሚስተዋሉ የመረጃ ጥራት ችግሮች፣ መንግስት በውድ ዋጋ ገዝቶ የሚያቀርቧቸው መድኃኒቶች ብክነት እንዲሁም ህገ ወጥነትን መከላከልና መቆጣጠር ከመቼውም በበለጠ በንቃት ሊሰራ እንደሚገባ ተብራርቷል።
የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራሞችን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ የተጀመሩ ተግባራትን መደገፍና ማጠናገር ከሁሉም የባለድርሻ አካላት የሚጠበቅ ትልቅ ኃላፊነት በመሆኑ ለዘርፉ ተገቢው ትኩረት ሊሰጥ ይገባልም ተብሏል።
ወረርሽኙን አሰመልክቶ ሰሞነኛ ርፖርት ቀርቦ ውይይት የተደሰገ ሲሆን በቀጣይ የተግባር ዕቅድ ላይም የትኩረት አቅጣጫ ተቀምጧል።
በምክክሩ ለተነሱ ሀሳብ እና አስተያየቶች ከሚመለከታቸው አካላት ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።
የዘገበው የዳውሮ ዞን ኮሚኒኬሽን ነው