የወባ ወረርሽኝ ለመከላከል እየተደረገ ያለውን ጥረት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ልደግፉ እንደሚገባ ተገለጸ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ም/ቤት ቋሚ ኮሚቴ ከክልል እና ዞን ጤና ተቋማት ጋራ በወባ ወረርሽኝ መከላከል ዙሪያ በቦንጋ ከተማ መክረዋል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ የኤች አይ ቪ መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መንግስቱ ኬተር እንዳሉት የወባ ወረርሽኝ ወደ ዜሮ ለማውረድ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የካፋ ዞን መንግስት ወረርሽኙን ለመግታት እያደረገ ያለውን ተግባር አመስግነው በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባም አሳስቧል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ም/ቤት የበጀት ፋይናንስና ኦዲት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ የኋላእሸት በላይነህ በበኩላቸው የወባ ወረርሽኝ በአሁን ላይ እየቀነስ መምጣቱን ገልጸዋል።
በዞኑ ውስጥ በጤና ዘርፍ በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ እየተመዘገበ ያለው ውጤት አበረታች እና ተሞክሮ ሊቀመር የሚችል ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልጸው ይህንን ተሞክሮ በሌሎች አካባቢዎች ላይ ማስፋት እንዳለብን ተናግረዋል።
የካፋ ዞን ጤና መምሪያ የወባ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ኮማንድ ፖስት አቶ አልማው ገ/ፃዲቅ የዞኑን አጠቃላይ የወባ ወረርሽኝ መከላከል አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።
የወባ ወረርሽኝ መከላከልና በአጎበር አጠቃቀም ዙሪያ ለበርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና የተሰጠ መሆኑን በሰነድ አመላክቷል።
የካፋ ዞን ም/ቤት የማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ አሚናት ሀሰን እንደገለጹት የወባ ወረርሽኝ ከመከላከል አንጻር የዞን ም/ቤት ከክልል ምክር ቤት እና የጤና ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ የጀመሩትን ተግባር አጠናክሮ እንደሚያስቀጥል ገልጸዋል ፡፡
የወባ ወርርሽኝ ከመከላከል አንጻር እየተደረጉ ያሉትን ጥረቶች ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት የካፋ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አክሊሉ አሰፋ ተናግረዋል።
የውይይት ተሳታፊዎች የወባ ወረርሽኝ እየቀነስ የመጣ ቢሆንም ስርጭቱን ለመግታት የሚመለከተው ባለድርሻ አካላት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ ገልጸዋል።
ዘገባው የካፋ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው