የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ የሰቆጣ ቃል ኪዳን ተግባሪ ወረዳዎች ጋር የ2016 ዓ/ም በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2017 ዓ/ም እቅድ ዙሪያ ምክክር አድርጓል ።
በሰቆጣ ቃልኪዳን የህጻናት መቀንጨር ከምግብ ስርአት ጋር ተያይዞ በርከት ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የክልሉ መንግስት ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት መመደቡም ታውቋል ፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ የሰቆጣ ቃል ኪዳን ተግባሪ ወረዳዎች ጋር የ2016 ዓ/ም በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2017 ዓ/ም እቅድ ዙሪያ በሚዛን አማን ከተማ ምክክር አድርጓል ።
በክልሉ ጤና ቢሮ የእናቶች ህጻናትና ስርዓተ ምግብ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መሰረት ወ/ማርያም በበኩላቸው ፕሮግራሙ ክልሉ ከተቋቋመ ከ2014 ዓ/ም ሲተገበር የመጣና የምግብ ዋስትና ክፍተት ያለባቸው 8 ወረዳዎች ተመርጠው በምግብ ዋስትና ራሳቸውን እንዲችሉ ሲሰራ እንደነበር ገልጸው አሁን ላይ 3 ወረዳዎች ተጨምረው 11 ወረዳዎች መድረሳቸውን ጠቅሰዋል።
በጥቂት የበጀት ድጋፍ ግንዛቤ በመፍጠር በችግሩ ውስጥ ያሉ ዜጎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ የፕሮግራሙ አላማ ሲሆን ተጠቃሚዎች የወተት ላም፣ በግና ፍየል፣ ዶሮ እንዲገዙ በማድረግ በቋሚነት ተጠቃሚ እየሆኑ እንደሆነም አቶ መሰረት ወ/ማሪያም ገልጸዋል።
የክልሉ ምግብና ስርዓተ ምግብ አስተባባሪና አቶ ማቴዮስ ማልዳዬ እንደገለጹት የመድረኩ ዓላማ በምግብ ስርአት ተጎጂ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን መሰረት በማድረግ የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም በቀጣይ 2017 ዓ/ም በሰቆጣ ቃልኪዳን እቅድ አቅዶ ወደተግባር ለመግባት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የክልሉ መንግስት የህፃናት መቀንጨርን ለመከላከልና የተመጣጠነ የአመጋገብ ስርዓትን ለማሻሻል የፈደራል መንግሰት ከሚመድበው ባጀት በተጨማሪም 11 ሚልዮን ብር ለዘርፉ በመመደብ mutching fund ድርሻውን መወጣቱን የገለፁት አቶ ማቴዎስ በ2017 ዓ ም ዕቅድ ዝግጅት ይህንን ባጀት ታሳቢ ተደርጎ በሽፋንም ይሁን በመጠን ጨምሮ እንደሚታቀድና ተጨባጭነት ያላቸው የማህበረሰብ ኑሮ ሊያሻሽል በሚችልና መቀንጨር ሊቀንስ በሚችሉ ተግባራት በትኩረት እንደሚታቀድ አብራርተዋል ፡፡
በሰቆጣ ቃልኪዳን የህጻናት መቀንጨር ከምግብ ስርአት ጋር በርከት ያሉ ችግሮችን ታሳቢ በማድረግ ለነፍሰጡር፣ ለሚያጠቡ እናቶችና ከ2 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት በፕሮግራሙ ተጠቃሚ እንዲሆኑና በዘላቂነት የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋልም ።
የሰቆጣ ቃል ኪዳን በክልላችን 11 ወረዳዎች ተግባራዊ እንደሚሆንና የምግብ ስርዓትና ስርዓተ ምግብ በክልላችን በሁሉም አከባቢ ተግባራዊ ሆኖ እየተሰራ መሆኑን አንስተው ዘርፉ የባለድርሻ ትብብርና ቅንጅት እንደሚፈልግም ጠቁመዋል ፡፡
ዘገባው የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።