የደቡብ ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ ጤናና ጤና ነክ ግብዓት ቁጥጥር ባለስልጣን በ2016 በጀት ዓመት ያከናወናቸው ተግባራትአፈጻጸም አበረታች መሆኑ ተገለጸ።

የአፈጻጸም ግምገማና የጤና ባለሙያዎች ፍቃድ በበይነ መረብ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር በታርጫ ከተማ ተካሂዷል።
በአፈጻጸም ግምገማ ላይ የተገኙት የደ/ም/ኢ/ህዝቦች ም/ቤት አፈ-ጉባኤ ክቡር አቶ ወንድሙ ኩርታ በመድረኩ ተገኝተው እንደገለጹት ጤና እና ጤና ነክ ግብአቶች አጠቃቀም በተቀመጠለት መስፈርት ለህ/ሰቡ እንዲቀርብ የቁጥጥር ስራ ተጠናክሮ መሰራት አለበት ብለዋል።
የቁጥጥር ስራን ውጤታማ ለማድረግ ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ በቀጣይ ቅንጅታዊ ስራ አጠናክረው ከባለድርሻ አካላት ጋር መስራት እንዳለበትም ክቡር አፌ ጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታ የገለጹት።
ባለፉት 2 ዓመታት በክልሉ ውስጥ በተከሰተው የወባ ወረርሽኝ ምክንያት በማድረግ በህገ-ወጥ መንገድ መድሀኒትና መገልገያ ቁሳቁሶች የሚታየው ዝውውር ችግር ተቀርፎ የመድሀኒቶች እና የመገልገያ ቁሳቁሶች ለታለመለት ዓላማ መዋል አለባቸው ብለዋል።
የክልሉ ጤና ቢሮ ጤና እና ጤና ነክ ግብዓት ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አሰፋ እንደገለጹት በ2016 ዓ/ም በባለስልጣኑ የተሰሩ የቁጥጥር እና የክትትል ስራዎች አበረታች በመሆናቸው የተመዘገቡ ጠንካራ ጎኖችን አጠናክረን ለማስቀጠል መረባረብ መቻል አለብን ብለዋል።
የክልሉ ጤና ቢሮ በአገር ደረጃ ባስመዘገበው አመርቂ አፈጻጸሞች በተሻለ ደረጃ ላይ የሚገኝ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ሙሉቀን ቢሮው በጠንካራ ጎን የተጠቀሱት አፈጻጸሞችን ለማስቀጠል እና በድክመት የተገመገሙትን ተግባራት የማረም ስራ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
የግል ጤና ተቋማት ለአገሎግሎቱ ከተፈቀደላቸው አቅም በላይ መድሀኒት መያዝ እና ህክምና አገልግሎት መስጠት ፣ ህገ-ወጥ የመድሀኒት አዘዋዋሪዎች ላይ እርምጃ የመውሰድ ስራ በሰፊው የተከናወነ ቢሆንም ከችግሩ ስፋት አኳያ አሁንም ቅንጅታዊ ስራን ይጠይቃል ያሉት አቶ ሙሉቀን በተለይ ጸረ ኮንትሮባንድ ግብረሃል ጋር በጋራ መስራት ይጠበቃል ብለዋል
ህገ-ወጥነትን ለማስቀረት በጤና ተቋማት የሚደረጉ መፍጨሮች ቢኖርም በጋራ ተባብሮ የመስራት እና የሚወሰደው እርምጃ አስተማሪ ከመሆን አንጻር አሁንም መስራትን ይጠይቃል ብለዋል።
የጤናና ነክ ስራዎች የሚመራበት ደንብ የክልሉ ጤና ቢሮ አዘጋጅቶ ለታችኛው የጤና መዋቅር የተላከ ሲሆን በቅርቡ የአፈጻጸም መመሪያ አዘጋጅተው ለመላክ በዝግጅት ላይ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
የክልሉ ም/ቤት ም/አፌ-ጉባ ወ/ሮ ጸሐይ ደርጫ ለጥና ስራ በቂ ትኩረት እኖዲሰጠው ለማድረግ በየእርከኑ ባሉ የህዝብ ምክር ቤት ጋር በጋራ መሰራት አለበት ብለዋል።
በመሆኑም ለምክር ቤት ቀርበው የሚወሰኑ ጉዳዮች በተደረጃ መረጃ ተደግፈው በመሆኑ የጤና ተቋማት የሚገጥሟቸውን ጉዳዮችን ትኩረት እንዲያገኝ መረጃን አደራጅተው በማቅረብ ከም/ቤቱ አባላት ጋር አብረው መስራት ይገባል ብለዋል።
በአፈፃፀም ግምገማው በቀረበው ሪፖርት እንደተገለጸው የቤንች ሸኮ ዞን ጤና ምሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ያከናወናቸው ተግባራት የተሻለና ሌሎች ዞኖች ተሞክሮ እንደሚሆን ተመላክቷል።
በቀረበው አፈጻጸም ሪፖርት ላይ አስተያየት ሰጭዎች እንደገለጹት በበጀት አመት የህክምና መሳሪያዎች በጥራት ወደ ህብረተሰቡ እንዲደርስ ለማድረግ የተሰራው የቁጥጥርና የክትትል ስራ የሚያበረታታ እንደሆነ ገልጸዋል።
ደረጃቸውን ያልጠበቁ የምግብ እና የመድሀኒት ምርቶች በተደረገው ቅንጅታዊ ስራ በአብዛኛው ዞኖች ተይዘው በአዘዋዋራዎቹ ላይ አስተዳደራዊ እና ህጋዊ ርምጃ መወሰድ መጀመሩ ለቀጣይ ክትትልና ቁጥጥር ስራ እንደሚያነሳሳቸውም ተናግረዋል።
በአፈጻጸም ግምገማ የክልሉ ም/ቤት ዋና አፈጉባኤ ክቡር አቶ ወንድሙ ኩርታ፣ ም/አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ጸሐይ ደርጫ፣ የም/ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች የፍትህ ተቋማት ሃላፊዎች እና ተወካዮች ፣ የጤና ቢሮ ማኔጅመንት አባላት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በግምገማ መድረኩ ተሳታፊ ሆነዋል።