የጤና መረጃዎችን ወደ ዲጂታል ስይስተም /online system/ ለማስገባት ስራ ለማስጀመር እየተራ መሆኑን የማሪ ማንሳ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት አስታወቀ።

በወረዳ ውስጥ በሁሉም ቀበሌዎች ላሉ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች መረጃ ለማሰባሰብና ለማሰራጨት የታቢሌት ስልክ መሰራጨቱም ታውቋል።
ጽ/ቤቱ አሁን በሥራ ላይ ላሉ ለሁሉም የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች አጠቃላይ የጤና መረጃ ወደ ዲጂታል ስይስተም /online system/ለማድረግ የክልል ጤና ቢሮ ከዞን ጤና መምሪያ ጋር በመሆን የታብሌት ስልክ /tablet phone /ለእያንዳንዱ ጤና ኤክስቴንሽን መሰራጨቱን የጤ/ጥ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በረከት ባቡሎ ተናግረዋል።
ታብለሌቱ አጠቃላይ የጤና መረጃዎችን ወደ Digitally system ለማስገባት፤ ፈጣን፣ ወቅታዊና ተአማኒ መረጃዎችንና ሪፖርቶችን ወደ ሚመለከተው ክፍል ለማድረስና በሚዲያ የዘመነ ጤና ባለሙያ እንዲፈጠር እንደሚያግዝም ተነግሯል ።
ቀጣይ በቅርብ ቀን ስለ ታቢለት ስልክ አጠቃቀም የጤና መረጃዎች እንዴት እንደሚመዘገብ እና ሪፓርት እንዴትስ እንደሚላክ አጭር ስልጠና እንደሚሰጥም ተነግሯል።
ዘገባው :-የማሪ ማንሳ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው ።