የጤና መድህን አገልግሎት መጠነኛ ግዴታ በመወጣት መጠነ ሰፊ የጤና አገልግሎት ማግኘት የሚያስችል የአገልግሎት ሥርዓት መሆኑ ተገለጸ።

በዳዉሮ ዞን ከጪ ወረዳ የህብረተሰቡን የማዐጤመ አገልግሎት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚቻልባቸዉ እና ፍጥነት መጨመር በሚያስችላቸዉ ጉዳዮች ላይ ልዩ ትኩረት እንዲደረግ የጋራ መግባባት መፍጠሪያ ዙሪያ የባለድርሻ አካላት ዉይይት ተካሂዷል ።
የከጪ ወረዳ የጤና ጥ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብዙአየሁ ዘርሁን የጤና መድህን አገልግሎት መጠነኛ ግዴታ በመወጣት መጠነ ሰፊ የጤና አገልግሎት ማግኘት የሚያስችል የአገልግሎት ሥርዓት ብለዋል።
አክሎም የማዐጤመ አገልግሎት አባላቱ በታመመ ቁጥር ከሚጠየቁ ከፍተኛ ወጪ በማዳን በትንሽ ወጭ ለመታከም የሚያበቃ እንደሆነም አብራርተዋል።
የወረዳዉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ህዝ/ግን/ፖለ/ሪዕ/ዓለ/ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተካልኝ ተፈራ ከዓለም አቀፋዊ፣ አህጉራዊ፣ ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታ ህ/ሰቡ ከሚጠየቀዉን ከፍተኛ ወጪ የመታደግ ዕድልንም የሚፈጥር ነዉ ብለዋል።
የወረዳዉ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዉለታዉ ሁሴን አባሉ ባዋጣዉ ገንዘብ ለራሱ እና ቤተሰቡ በዓመቱ ታሞ ባይታከም እንኳ ለወገኑ በጎነትን ማድረግ እንደሆነም አስረድተዋል።
በመጨረሻም አስተዳዳሪዉ ማዐጤመ አባልነት አንድ ሰው ጠነኛ ሆኖ ባለበት ጊዜ ለራሱ እና ለወገን የሚያስቀምጥ የነጌ ስንቅ ሂደትን ተከትሎ የሚፈጸም በመሆነለ ሁሉም አባል ሆኖ ተጠቃሚ እንዲሆን ጥሪ አስተላልፈዋል።
ዘገባዉ፣ የከጪ ወረዳ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነዉ።